Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ሕይወትህ ሕይወቴ

Hiwoteh Hiwotie

2017 · ትራክ 1 · 4:34 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

kእኖራለሁ ባንተ እንቀሳቀሳለሁ

በልቼ ጠጥቼ ወጥቼ ገባለሁ

ተኝቼ ደግፈኸኝ ከእንቅልፌ ነቃለሁ

ደግሞ ባዲስ ምህረት አዲስ ቀን መራለሁ

ባንተ ነው መኖሬ መኖሬ - ባንተ ነው መኖሬ (፪x)

ባንተ ነው መሄድ መቀመጤ - ባንተ ነው መኖሬ

ባንተ ነው መዋሌ ማደሬ - ባንተ ነው መኖሬ

ባንተ ነው መውጣቴ መግባቴ - ባንተ ነው መኖሬ

ባንተ ነው መቆም መነሳቴ - ባንተ ነው መyኖሬ

ሕይወቴ ሕይወትህ ካንተ የተቀበልኩት አለው ልዩ ትርጉም

ሕይወትህ ሕይወቴ ካንተ K በዚህ አይለካም

የሕይወት እስትንፋስ ካንተ አግኝቻለሁ

መኖር ደስ እያለኝ እንድኖር ሆኛለሁ

የሕይወት እስትንፋስ ካንተ አግኝቻለሁ

መኖሬን ወድጄው እንድኖር ሆኛለሁ

ሰሪዬ ነህ አንተ ፈጣሪዬ መገኛዬ

የህይወት ምንጭ ነህ መኖሪያዬ

ሰሪዬ ኢየሱስ ፈጣሪዬ መገኛዬ

የሕይወት ምንጭ ነህ መኖሪያዬ

መሄድ መቀመጤ መቆም መነሳቴ

በእጅህ አይደል ወይ መላው እኔነቴ ፈጠርከኝ አኖርከኝ

እኔ ያንተ መቅደስ አንተም መኖሪያዬ

ቤቴም ያንተ ቤት ነው እጅህ አለኝታዬ ፈጠርከኝ አኖርከኝ

ሰሪዬ ነህ አንተ ፈጣሪዬ መገኛዬ

የሕይወት ምንጭ ነህ መኖሪያዬ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ