ክብር ክብር ክብር
Keber Keber Keber
ትራክ 5 · አማርኛ
:አዝ፦ ክብር ክብር ክብር
ጌታ ለአንተ ይሁን በሰማይ በምድር
መካኒቱን በልጅ የባረካት
ደስ የተሰኘች ሴት ያደረካት
ምስኪኑን ከአመድ ያነሳኸው
ለሹመት ሽልማት ያበቃኸው
:አዝ፦ ክብር ክብር ክብር
ባሕሩን ለሁለት የከፈልከው
ሾላውን ከስሩ የነቀልከው
ለደካማው ኃይልን የሰጠኸው
በከፍታዎች ላይ ያራመድከው
:አዝ፦ ክብር ክብር ክብር
ዘንዶውን የወጋህ የቆራረጥክ
ጠንካራውን አለት የሰነጠክ
የተራበችውን ነፍስ ያጠገብክ
የተበተኑትን የሰበስብክ
ክብር ለአንተ ይሁን
:አዝ፦ ክብር ክብር ክብር
የእስረኞችን ጩኸት አዳምጠሃል
የወህኒውን መዝጊያ ሰባብረሃል
ሰው የረሳቸውን አስታውሰሃል
ያልጋ ቁራኞችን ፈውሰሃል
ክብር ለአንተ ይሁን
:አዝ፦ ክብር ክብር ክብር
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ