ሶስት መንገድ የለም
Sost Menged Yelem
ትራክ 8 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ያዝ ለቀቅ ሔድ መጣ ገባ ወጣ
ሕይወት ትርጉም ሲያጣ
ወይ ከየሱስ ወይ ከዓለም ምረጥ እንጂ
ሦስት መንገድ የለም
እንጀራ ለመብላት ሺ ተሰበሰበ
መስቀል ለመሸከም አንድም አልቀረበ
ተዓምር ለማየት እልፍ ሰው ቢንጋጋ
ኢየሱስ ብቻ ነው በጦር የተወጋ
አዝማች · Chorus
:አዝ፦ ያዝ ለቀቅ
ቁጥር 2 · Verse 2
በየመንገድ ወራጅ ሞልቷል ተሳፋሪ
ከጠጣ በኋላ ወጭቱን ሰባሪ
ትላንትን አትርሳ አትሁን ውለታ ቢስ
ገባ ወጣ አትበል ጸንተህ ቁም በየሱስ
አዝማች · Chorus
:አዝ፦ ያዝ ለቀቅ
ቁጥር 3 · Verse 3
ድንኳን አስከሚወርድ ድግስ ተጠናቆ
ስደት አስኪመጣ ነጻው ዘመን አልቆ
ስንት ሰው ዘምሯል ስንቱስ አጨብጭቧል
በመከራው ቀን ግን ጌታ ብዙዎችን ታዝቧል
አዝማች · Chorus
:አዝ፦ ያዝ ለቀቅ
ቁጥር 4 · Verse 4
እራሱን ላይገዛ ላይችል መታዘዙን
በሞቅታ ጊዜ ቃል ኪዳነ ብዙ
ሆኖለት ላይከፋል ስለት የተሳለ
አሁን በዚህ መሃል ባለዳ ስንት አለ?
አዝማች · Chorus
:አዝ፦ ያዝ ለቀቅ
ቁጥር 5 · Verse 5
መና ካዘነበ ከምንጩ ካጠጣን
ከአመድ አንስቶን ከረግረግ ካወጣን
ካበላን ካጠጣን ካከበረን ኋላ
መስቀሉን አንሽሽ አብረን እንጉላላ
አዝማች · Chorus
:አዝ፦ ያዝ ለቀቅ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ