ታሪኬ የጀመረው
Tarikie Yejemerew
ትራክ 7 · 6:09 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ታሪኬ የጀመረው
በቀራኒዮ ነው
በመስቀሉ ግርጌ
አጋጣሚ አይደለም
መወለድ ማደጌ
ሠይጣን ሲቀጠቀጥ
እራሱ ሲመታ
ባርነቴ ሲሻር
ሰንሰለት ሲፈታ
ጠላት ሲመሽበት ለእኔ ግን ሲነጋ
ይኼ ውብ ታሪኬ ተጀመረ እዚያጋ
ምሥጋናዬ
ምሥጋናዬ ይኼው ለጌታዬ
ምሥጋናዬ
ምሥጋናዬ ይኼው በዜማዬ
ከወህኒ ከፍርድ
እኔኑ ሊያወጣ
ከድንግል ማርያም
ሥጋ ነስቶ መጣ
መልክ ውበቱን ተወ
የባርያን መልክ ያዘ
እስከ መስቀል ሞትም
በፍቅር ታዘዘ
ከአደረገው በቀር ኢየሱሴ ምንም ታሪክ የለኝ የእራሴ
አዝማች · Chorus
ታሪኬ የጀመረው በቀራኒዮ ነው
በመስቀሉ ግርጌ በአጋጣሚ አይደለም መወለድ ማደጌ
ቁጥር 2 · Verse 2
ሠይጣን ሲቀጠቀጥ እራሱ ሲመታ
ባርነቴ ሲሻር ሰንሰለት ሲፈታ
ጠላት ሲመሽበት ለእኔ ግን ሲነጋ
ይኼ ውብ ታሪኬ ተጀመረ እዚያጋ
ምሥጋናዬ ምሥጋናዬ ይኼው ለጌታዬ
ምሥጋናዬ ምሥጋናዬ ይኼው በዜማዬ
በቃሉ እውነተኛ
በተግባሩም ደግ
ከፋት የሌለበት
የእግዚአብሔር በግ
እኔን ሊያዘምረኝ እርሱ አለቀሰ
እኔን ሊያከብረኝ ውረደትን ለበሰ
ከሥም ሁሉ በላይ ሥም አለው
ዛሬም ምሥጋናዬ ለእርሱ ነው
አዝማች · Chorus
ታሪኬ የጀመረው በቀራኒዮ ነው
በመስቀሉ ግርጌ በአጋጣሚ አይደለም መወለድ ማደጌ
ቁጥር 3 · Verse 3
ሠይጣን ሲቀጠቀጥ እራሱን ሲመታ
ባርነቴ ሲሻር ሰንሰለት ሲፈታ
ጠላት ሲመሽበት ለእኔ ግን ሲነጋ
ይኼ ውብ ታሪኬ ተጀመረ እዚያጋ
ምሥጋናዬ ምሥጋናዬ ይኼው ለጌታዬ
ምሥጋናዬ ምሥጋናዬ ይኼው በዜማዬ
ብዙ የነበረውን
እዳዬን ሻረልኝ
ኃጢአቴን በሁሉ ከኋላው ጣለልኝ
በመስቀል ጠርቆ
ከእኔ አስወግዶ
ጨካኙን ከሳሼን
ባዶ እጁን ሰደደው
እዛጋ ጀመረ ታሪኬ
ምሥጋና ይብዛለት አምላኬ
አዝማች · Chorus
ታሪኬ የጀመረው በቀራኒዮ ነው
በመስቀሉ ግርጌ በአጋጣሚ አይደለም መወለድ ማደጌ
ቁጥር 4 · Verse 4
ሠይጣን ሲቀጠቀጥ እራሱን ሲመታ
ባርነቴ ሲሻር ሰንሰለት ሲፈታ
ጠላት ሲመሽበት ለእኔ ግን ሲነጋ
ይኼ ውብ ታሪኬ ተጀመረ እዚያጋ
ምሥጋናዬ ምሥጋናዬ ይኼው ለጌታዬ
ምሥጋናዬ ምሥጋናዬ ይኼው በዜማዬ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ