ጌታ ሆይ አትመጣም ወይ
Gieta Hoy Atmetam Hoy
ትራክ 2 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በእሳት ቁጥቋጦ የተገለጥከው
የአብርሃም የይስሐቅ የያዕቆብ አምላክ ነኝ ያልከው
መርዛሙን እባብ በትር ያደረክ
በመስኪን ነገር ባሕሩን የከፈልክ
መርዙን አውጣልን ከበትራችን
መድሃኒት አርገን ለምድራችን
አዝማች · Chorus
ጌታ ሆይ የሱስ ሆይ
ጌታ ሆይ አትመጣም ወይ
ቁጥር 2 · Verse 2
ጽድቅን ያደረግን እየመሰለን
ባዶ ቅንአት እያቃጠለን
የሕሊናን ድምጽ ተግሳጽን ንቆ
እግራችን ሲሮጥ ወደ ደማስቆ
በጽድቅ ጸሐይ ተገለጠልን
የእይናችንን ቅርፊት ጣልልን
አዝማች · Chorus
ጌታ ሆይ የሱስ ሆይ
ጌታ ሆይ አትመጣም ወይ
ቁጥር 3 · Verse 3
ፍቅራችን ያንገት የለበጣ ነው
ከአንተ አይደለም ከየት አመጣነው
አንዱን ከሌላው እንለያለን
ልብን አይደለም ልብስ እናያለን
ልባችን ጨካኝ ለሰው አይራራ
ዳስልንና ዓይናችን ይብራ
አዝማች · Chorus
ጌታ ሆይ የሱስ ሆይ
ጌታ ሆይ አትመጣም ወይ
ቁጥር 4 · Verse 4
የዕምነት አባቶች የቀደሙቱ
ለፍቅር ኖረው ለፍቅር ሞቱ
ታሪክ አንባቢ ሆነን ቀርተናል
ከአንተ በስተቀ ማን ይችለናል
የነሱ አምላክ ዛሬም ሕያው ነህ
እባክህ ጐብኘን ለስምህ ብለህ
አዝማች · Chorus
ጌታ ሆይ የሱስ ሆይ
ጌታ ሆይ አትመጣም ወይ
ቁጥር 5 · Verse 5
እሳትህ ቢነድ እንነጥራለን
መዶሻ ብትልክ እንሰባበራለን
ውኃ ብታፈስ እንጸዳለን
ዝም ካልከን ግን እንጐዳለን
ዛሬም ወዳንተ መጥተናልና
ቤትህን ሙላ በክብር ዳመና
አዝማች · Chorus
ጌታ ሆይ የሱስ ሆይ
ጌታ ሆይ አትመጣም ወይ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ