ክብር ይሁን
Keber Yihun
2010 · ትራክ 3 · 19:21 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ክብር ይሁን ክብር x8
በላይ በሰማይ ዙፋኑ ላይ
በታች በምድር ለእግዚአብሔር
ክብር ይሁን ክብር x4
ሀጢያተኛውን አስበኸዋል
በደምህ አጥበህ አንፅተኸዋል
ከፃድቃን ማህበር ቀላቅለኸዋል
ከሳሹ ጠላት ዲያብሎስ አፍሮአል
ለዚህ ለስራህ ምን ይከፈላል
ክብር ይሁን ክብር x2
በላይ በሰማይ ዙፋኑ ላይ
በታች በምድር ለእግዚአብሔር
ክብር ይሁን ክብር x4
ደረቁን ምድር አረስርሰሀል
የተራቆተውን አንተ አልብሰሀል
በታሪክ ማህደር ያልታወቀውን
አንተ አስጠግትህ አገነንክ ስሙን
ጌታዬ ክብሩ ለአንተ ይሁን
ዙፋኑ ከጥንት ከዘላለም
ብርቱ ተዋጊ እንዳንተ የለም
የጠላት ምክሩን አፍርሰኸዋል
ባንድላይ መጥተው ተበትነዋል
ጌታ ሆይ ላንተ ክብር ይገባሀል
ክብር ይሁን ክብር x2
በላይ በሰማይ ዙፋኑ ላይ
በታች በምድር ለእግዚአብሔር
ክብር ይሁን ክብር x4
አዝማች · Chorus
በኃይል ቢሆን እንዳንተ ማነው ኃይል
በክብር ቢሆን እንዳንተ ማነው ክቡር
በስልጣን ቢሆን እንዳንተ ማነው ባለስልጣን
እግዚአብሔር እግዚአብሔር ኃያል (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ክብር ይሻራል ውበት ይጠፋል
ሃብትም ይበናል
አበባው ረግፎ ሲጠወላልግ
ትላንት ያየነው ለዛሬ ሲደርቅ
አንተ ብቻ አትለዋወጥ
እጅግ ዕጹብ ድንቅ
አዝማች · Chorus
በኃይል ቢሆን እንዳንተ ማነው ኃይል
በክብር ቢሆን እንዳንተ ማነው ክቡር
በስልጣን ቢሆን እንዳንተ ማነው ባለስልጣን
እግዚአብሔር እግዚአብሔር ኃያል (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በምድር ክበቦች ላይ የሚራመድ
ሰማይ ተቀምጦ ምድር የሚረግጥ
ከፍ ካለው በላይ ከፍ ያለ ጌታ
እንዳንተ ማነው በቀን በማታ
አንተ ብቻ ትላንትም ዛሬም የሁሉ ጌታ
የእስራኤል ታቦት ጠላቶች ማርከውት
አማሌቅ መሃል ይቀመጥ ብለው
አማልክት ሁሉ ሲሰባበሩ
ዳጐን ሲወድቅ ሲናቅ ባገሩ
የእስራኤል ታቦት በአሸናፊነት ገባ በክብሩ
አዝማች · Chorus
በኃይል ቢሆን እንዳንተ ማነው ኃይል
በክብር ቢሆን እንዳንተ ማነው ክቡር
በስልጣን ቢሆን እንዳንተ ማነው ባለስልጣን
እግዚአብሔር እግዚአብሔር ኃያል (4x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ