Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ማራናታ

Maranatha

2012 · ትራክ 4 · 4:49 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ዘመኑ አብቅቶ አልቆ ሰዓቱም ደርሷል

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መምጫ

በቶሎ መጣለሁ ልክ እንዳለው

እርሱ በደጅ ነው (፪x)

እንግዲህ የተዘጋጀው

ጌታውን ታምኖ የጠበቀው

ለእርሱ በቶሎ ይመጣል

ሽልማቱን ሊሰጠው

አሜን ጌታ ኢየሱስ ማራናታ (፬x)

አሜን ማራናታ ጌታ ሆይ ና (፬x)

አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር

እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያዘጋጀው

ከነሱ ጋር አብሮ በአንድ ላይ ሊኖር

እርሱ በደጅ ነው

እንግዲህ የተዘጋጀው

እድፉንም በደሙ ያነጻው

እርሱ በዚያ ይኖራል

የንጉሡን ፊት እያየው

አሜን ጌታ ኢየሱስ ማራናታ (፬x)

አሜን ማራናታ ጌታ ሆይ ና (፬x)

ና ይበል ጠቢብ የሆነ

ነፍሱን ከእሳት ሊያድን የወደደ

የሚያድነን አዳኝ ከአብ የተላከ

ኢየሱስ አለ አይዞህ ጋብዘው ወዳንተ

አሜን ማራናታ ጌታ ሆይ ና (፬x)

አሜን ጌታ ኢየሱስ ማራናታ (፬x)

አሜን ማራናታ ጌታ ሆይ ና (፬x)

አሜን ጌታ ኢየሱስ ማራናታ (፬x)

አሜን ማራናታ ጌታ ሆይ ና (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ