ለአንተ ብቻ
Lante Becha
2012 · ትራክ 1 · 6:06 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ለአንተ ብቻ (፯x)
ለአንተ ብቻ (፯x)
በዚህ ምድር ላይ
ስለ ብዙ ነገር ይተረካል
ለሕያውም ለግዑዙም ዜማ ይቀመራል
ሁሉም በእራሱ መንገድ ይጓዛል ይሮጣል
የወደደውን መርጦ ያወድሳል
አዝማች · Chorus
እኔ ግን ከሁሉም አንተን መርጫለሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
በዘመኔ ሁሉ እቀኝልሃለሁ
የእኔ ዜማ ዝማሬ የሚገባው
የመዳኔ ብቸኛ መንገድ የሆንህ
ለአንተ ብቻ (፯x)
ለአንተ ብቻ (፯x)
ለአንተ ብቻ (፯x)
ለአንተ ብቻ (፯x)
አንዱም ተነሳ የዜማ እቃውን ቃኘ
ድምፁን ከፍ አድርጐ ለሚያልፈው ተቀኘ
ሌሎችም አብረው በአንድነት ተስማምተው
(ሁሉም በአንድ ልብ ህብረት ሆነው)
ውዳሴን አሰሙ ለሚያልፈው
አዝማች · Chorus
እኔ ግን ኢየሱስ አንተን መርጫለሁ
ቁጥር 3 · Verse 3
በዘመኔ ሁሉ እቀኝልሃለሁ
የእኔ ዜማ ዝማሬ የሚገባው
የመዳኔ ብቸኛ መንገድ የሆንህ
ለአንተ ብቻ (፯x)
ለአንተ ብቻ (፯x)
ለአንተ ብቻ (፯x)
ለአንተ ብቻ (፯x)
ኦዎኦ (፲፪x)
ምሥጋናዬ (ኦ)
አምልኮዬን (ኦ)
አቀርባለው ለአንተ ዝማሬዬን (፮x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ