Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ጠብቀኝ

Tebeqegn

2014 · ትራክ 6 · 4:16 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ከሰማይ ሰማይ ወረደ

እንደ በግ ለእኔ ታረደ

ኢየሱስ ስለእኔ ታረደ

መች አንዲህ ቀላል ነው ነገሩ

የኢየሱስ የመስቀል ላይ ጣሩ (፪x)

አበሳዬን ወሰደው ከላዬ

የእኔ ኢየሱስ በሃፍረት መታያዬ

ድፍረት ሆነኝ መግባት ወደ አባቱ

አስታረቀኝ በመስቀል ላይ ሞቱ

አማለደኝ በመስቀል ላይ ሞቱ (፪x)

የህማም ሰው ሆነ ደቀቀ

ኢየሱስ ስለእኔ ታመመ (፪x)

መራራውን ጽዋዬን ጠጣ

ሊያተርፈኝ ከሚመጣው ቁጣ

ሊያድነኝ ከሚመጣው ቁጣ

አበሳዬን ወሰደው ከላዬ

የእኔ ኢየሱስ በሃፍረት መታያዬ

ድፍረት ሆነኝ መግባት ወደ አባቱ

አስታረቀኝ በመስቀል ላይ ሞቱ

አማለደኝ በመስቀል ላይ ሞቱ (፪x)

ይቅር በላቸው አባ ማራቸው

ይህን ሁሉ ግፍ አትይባቸው

ብለህ ማልደሃል በዛ ፈተናህ

የሚያደርጉትን አያውቁምና

ከሙታን በኩር ነህ

ሞትን ድል የነሳህ

በአባትህ ቀኝ አለህ

የይሁድ አምበሳ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ