Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

በል ተቀበለኝ

Bel Teqebelegn

2014 · ትራክ 5 · 3:46 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በል ተቀበለኝ ኢየሱስ መጥቻለሁ

መንገዴ በዝቶብኝ ደክሜያለሁ

ምሕረትህ ከሕይወት በእውነት ይሻላልና

ማረኝ ልበልህ አባ እንደገና

ላይሞላልኝ ላይሳካልኝ

ከእቅፍህ ምን አወጣኝ

ለውድቀቴ ምክንያቱን ደርድሬ

ይቆጨኛል ሳስበው ዛሬ

በል ተቀበለኝ ኢየሱስ መጥቻለሁ

መንገዴ በዝቶብኝ ደክሜያለሁ

ምሕረትህ ከሕይወት በእውነት ይሻላልና

ማረኝ ልበልህ አባ እንደገና

በሚመለስ ደስ ይልሃልና

ፊትህ መጣሁ ይኸው እንደገና

ክብር የለም ውርደት ነው ዓለም ያለው

ከአንተ ጋራ መኖር ሰላም ነው

በል ተቀበለኝ ኢየሱስ መጥቻለሁ

መንገዴ በዝቶብኝ ደክሜያለሁ

ምሕረትህ ከሕይወት በእውነት ይሻላልና

ማረኝ ልበልህ አባ እንደገና

ከህልውናህ ሚሻል ምን አለና

መገኘትህ በቂ ነውና

እህል ውኃ ሞልቶ ሳይጐለኝ

ክብርህ ጌታ ውስጤን ራበኝ

በል ተቀበለኝ ኢየሱስ መጥቻለሁ

መንገዴ በዝቶብኝ ደክሜያለሁ

ምሕረትህ ከሕይወት በእውነት ይሻላልና

ማረኝ ልበልህ አባ እንደገና

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ