ተመሥገን ጌታዬ
Temesgen Gietayie
ትራክ 9 · 3:38 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ተመሥገን ጌታዬ
ክብር ገናንነት ለሥምህ ይሁን
ተመሥገን ኢየሱስ ሆይ
ክብር ገናንነት ለሥምህ ይሁን (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
በጉለት እንዲቆይ ሳይደክም ጉልበቴ
ኃይልን አስታጠቀኝ ከላይ መድኃኒቴ
በብዙ ውሽንፍር ቢያጥለቀልቅ ጐርፉ
ጠላቶች በአንተ ሥም ሁሉም ተሸነፉ
አዝማች · Chorus
ተመሥገን ጌታዬ
ክብር ገናንነት ለሥምህ ይሁን
ተመሥገን ኢየሱስ ሆይ
ክብር ገናንነት ለሥምህ ይሁን (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የኑሮዬ ተገን ክብሬ መከታዬ
ኃይሌም ይታደሳል አንተ ነህ ተድላዬ
ማዕበሉ ተነስቶ ሊያሰጥመኝ ሲቃጣ
በገሀድ አያለሁ ረዳቴ ስትመጣ
አዝማች · Chorus
ተመሥገን ጌታዬ
ክብር ገናንነት ለሥምህ ይሁን
ተመሥገን ኢየሱስ ሆይ
ክብር ገናንነት ለሥምህ ይሁን (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የእግዚአብሔር ቸርነት አያልቅም ቢቆጠር
ነነዌም ብትሰራ ኃጢአት በማግበስበስ
አምላክም አስቦ እነርሱን ለመምከር
አዘዘው ዮናስን ለሕዝቡ እንዲናገር
አዝማች · Chorus
ተመሥገን ጌታዬ
ክብር ገናንነት ለሥምህ ይሁን
ተመሥገን ኢየሱስ ሆይ
ክብር ገናንነት ለሥምህ ይሁን (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ