Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የእኔ ጌታ

Yenie Gieta

ትራክ 11 · 4:13 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ጌቴ ኢየሱስ የእኔ ቤዛ

ጉስቁልናዬ ቢበዛ

ከክብሩ ተዋረደልኝ

በእኔ ፈንታ ታረደልኝ (፪x)

የእኔ ጌታ ስለ እኔ ገዶት

ኃጢአቴም አስጨንቆት

ዝም ብሎ እንደ ጠቦት

በሀሰት ተመስክሮበት በችሎት

ዕዳዬን ከፍሎታል ተሰቅሎ በመሞት

ግብዝ አይደል እንደ ሰው

ወረት ጨርሶ ያልነካው

በጐልጐታ ላይ የታየው

እውነትም እርሱ ፍቅር ነው (፪x)

የእኔ ጌታ ስለ እኔ ገዶት

ኃጢአቴም አስጨንቆት

ዝም ብሎ እንደ ጠቦት

በሀሰት ተመስክሮበት በችሎት

ዕዳዬን ከፍሎታል ተሰቅሎ በመሞት

ያጀቡት ሁሉ ፈርጥጠው

ለሰይፍ ለጐመድ አጋልጠው

በዚያን ምሽት አልቦታል

ቃቶ ነፍሴን ታድጓታል (፪x)

የእኔ ጌታ ስለ እኔ ገዶት

ኃጢአቴም አስጨንቆት

ዝም ብሎ እንደ ጠቦት

በሀሰት ተመስክሮበት በችሎት

ዕዳዬን ከፍሎታል ተሰቅሎ በመሞት

በግፍ ጀርባው ተላልጦ

እግሩንም ለስቃይ ገልጦ

ንጹስህ ደሙን ለእኔ ከፍሎ

በቀራንዮ ደርቆ ውሎ (፪x)

የእኔ ጌታ ስለ እኔ ገዶት

ኃጢአቴም አስጨንቆት

ዝም ብሎ እንደ ጠቦት

በሀሰት ተመስክሮበት በችሎት

ዕዳዬን ከፍሎታል ተሰቅሎ በመሞት

ይህ ፍቅር በሕይወቴ ገብቶ

የደህንነት ሥራ ሰርቶ

ቆሻሻነቴን ቀይሮ

አይቻለሁኝ ውብ ኑሮ (፪x)

የእኔ ጌታ ስለ እኔ ገዶት

ኃጢአቴም አስጨንቆት

ዝም ብሎ እንደ ጠቦት

በሀሰት ተመስክሮበት በችሎት

ዕዳዬን ከፍሎታል ተሰቅሎ በመሞት

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ