የሠራዊት ጌታ
Yeserawit Gieta
ትራክ 5 · 3:40 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የሠራዊት ጌታ ኃያሉ መድህኔ
ሲጠብቀኝ ሳለ ፍርድና ኩነኔ
በኃጢአት ጣር ስኖር ተሳስሬ
ከእስራቴ ፈታኝ መራኝ ወደ አገሬ (፪x)
አዝማች · Chorus
በጭንቄ ተጨንቆ መስቀል ላይ ተሰቅሎ
ላረባሁት ልጁ እንዲያ ተጐሳቁሎ
ደሙን አፈሰሰ በፍቅሩ ተገዶ
ሕይወቴን አዳናት ስለ እኔ ተዋርዶ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ፍፁም የማልረባ ማስተዋል የሌለኝ
አዳኜን የማላውቅ ፍርድ የሚጠብቀኝ
የሰይጣን ምርኮኛ ሸክም የተጫነኝ
እንዲህ ያለሁ ነበር ጌታ ሳያገኘኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
በጭንቄ ተጨንቆ መስቀል ላይ ተሰቅሎ
ላረባሁት ልጁ እንዲያ ተጐሳቁሎ
ደሙን አፈሰሰ በፍቅሩ ተገዶ
ሕይወቴን አዳናት ስለ እኔ ተዋርዶ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ፍርሃት መጠራጠር ክፋትና እርኩሰት
ይወገድ ትዕቢት ቅናት ምቀኝነት
ተንኮልና ውሸት ሀሜት ክፉ ምኞት
ተደምስሰው ይጥፉ በጽዮኑ አለት (፪x)
ይውደቁ ይፈጩ ይድቀቁ በአንድነት
ቀንበሩ ተሰብሯል ይቅርብኝ ባርነት
ዕዳዬም ተከፍሎ ታውጇል አርነት
ሞትም አያስፈራኝ ተሰጥቶኛል ሕይወት (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ