ርዕስ
Title
2010 · ትራክ 1 · አማርኛ
አዳኜ ኢየሱስ ገናናው
የእጄን ሰንሰለት በጠሰው
ተመስገን ልበል ልቀኝለት
በእግሩ ሥር ልውደቅ
ልስገድለት ይህም አነሰበት
ነፍሴን አስጨንቋት የጠላቴ ጩኸት
አይኖቼን ባቀና ከላይ ስመለከት
ከመቅደሱ ሆኖ እምባዬን አበሰ
ያሰረኝን ገመድ ጌታ በጣጠሰ
አዳኜ ኢየሱስ ገናናው
የእጄን ሰንሰለት በጠሰው
ተመስገን ልበል ልቀኝለት
በእግሩ ሥር ልውደቅ
ልስገድለት ይህም አነሰበት
የሞት ቀንበር ከቦኝ ያመፅ ፈሳሽ ውጦኝ
ሲኦል አፉን ከፍቶ ባጥንቴ አስቀርቶኝ
ስሞታ ነገርኩኝ ላምላኬ ሳልሰለች
እግዚአብሔር ተቆጣ ምድር ተናወጠች
አዳኜ ኢየሱስ ገናናው
የእጄን ሰንሰለት በጠሰው
ተመስገን ልበል ልቀኝለት
በእግሩ ሥር ልውደቅ
ልስገድለት ይህም አነሰበት
ጠላቴን ሰበረ እንዳያንሰራራ
ከቁጣው ጢስ ወጣ ፍምም ከሱ በራ
ባእድ የረገጠኝ እንደመንገድ ጭቃ
ነፃነቴን ሰጠኝ መቆዘሜ አበቃ
አዳኜ ኢየሱስ ገናናው
የእጄን ሰንሰለት በጠሰው
ተመስገን ልበል ልቀኝለት
በእግሩ ሥር ልውደቅ
ልስገድለት ይህም አነሰበት
ዛሬማ ሰው ሆኜ ቀስት እገትራለሁ
በኮረብታ ቆሜ ምሥጋና እሰዋለሁ
ፅኑ እግር ለሰጠኝ የማይንሸራተት
ለናዝሬቱ ኢየሱስ እጥፍ ልስገድለት
አዳኜ ኢየሱስ ገናናው
የእጄን ሰንሰለት በጠሰው
ተመስገን ልበል ልቀኝለት
በእግሩ ሥር ልውደቅ
ልስገድለት ይህም አነሰበት
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ