የሚመጣ
Yemimeta
2010 · 3:47 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የሚመጣ የሚከብር የሚነግስ ኢየሱስ
ቁጥር 1 · Verse 1
ተቀናቃኝ የለው ወይም ባላጋራ
ፊት ለፊት የሚቆም ግጥሚያ ከርሱ ጋራ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በአህዛብ ፊት ሊከብር በድንቅ ይገለጣል
ብንወድም ባንወድም ኢየሱስ ይነግሳል (፪x)
አዝማች · Chorus
የሚመጣ የሚከብር የሚነግስ ኢየሱስ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ከእንግዲህ ለውርደት ለሞት አይሰጥም
አንድ ጊዜ በመስቀል ፈጽሟል ሁሉንም (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ያነ እዳ ሊከፍል ዛሬ ዳኛ ሆኖ
ይመጣል ጌታችን በክብር ተክኖ (፪x)
አዝማች · Chorus
የሚመጣ የሚከብር የሚነግስ ኢየሱስ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ከዘመናት በፊት ሁሉን ጥለው ያሉ
ለርሱ የተገዙ ሞፈር ቀንበር ሳይሉ (፪x)
ቁጥር 6 · Verse 6
በታላቅ እልልታ በሆታ በደስታ
በአይናቸው ያዩታል የዘላለሙን ጌታ (፪x)
አዝማች · Chorus
የሚመጣ የሚከብር የሚነግስ ኢየሱስ (፪x)
ቁጥር 7 · Verse 7
ከደመናው መሃል ግርማው የሚያስፈራ
በመላዕክት ታጅቦ ከአገልጋዮች ጋራ (፪x)
ቁጥር 8 · Verse 8
የቅዱሳን አባት ስሙም አማኑኤል
በከዋክብት ደምቆ አሜን ከተፍ ይላል (፪x)
አዝማች · Chorus
የሚመጣ የሚከብር የሚነግስ ኢየሱስ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ