ይቅርታን ለማድረግ
Yeqertan Lemadreg
2010 · ትራክ 8 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ምህረትህ በእኔ ላይ እንድሆን እሻለሁ
እኔ ግን በቀልን ወዳጅ አድርግያለሁ
ነፍሴ ተጎሳቁላ ፍጹም ሳያምርባት
ተኮንና እንዳትኖር ይቅርታን አስተምራት
አዝማች · Chorus
ይቅርታን ለማድረግ ልቤ አልሆን እያለው
እግሬ የሚራመደው ሸካራ መንገድ ነው
የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ ድካሜን ታውቃለህ
ዳብሰኝ እንደገና ትለውጠኛለህ
ቁጥር 2 · Verse 2
ወንድሜን ማቁሰሌ እጅግ ይረሳኛል
የተበደልኩትን መቁጠር ይጥመኛል
ምን አለበት ዛሬ ልቤን ብትጠርበው
መቀጥቀጫው ብረት መዶሻው በእጅህ ነው
አዝማች · Chorus
ይቅርታን ለማድረግ ልቤ አልሆን እያለው
እግሬ የሚራመደው ሸካራ መንገድ ነው
የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ ድካሜን ታውቃለህ
ዳብሰኝ እንደገና ትለውጠኛለህ
ቁጥር 3 · Verse 3
እጄን ለአንተ ሰጠው አንተ እንድታስተምረኝ
ለውጠኝ ጌታ ሆይ ይሄው በፊትህ ነኝ
የበደለኝን ሰው ይቅር ብዬ እንዳልፈው
በቀልን ሳላስብ በፍቅር እንዳቅፈው
አዝማች · Chorus
ይቅርታን ለማድረግ ልቤ አልሆን እያለው
እግሬ የሚራመደው ሸካራ መንገድ ነው
የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ ድካሜን ታውቃለህ
ዳብሰኝ እንደገና ትለውጠኛለህ
ቁጥር 4 · Verse 4
ምህረትህ በእኔ ላይ እንድሆን እሻለሁ
እኔ ግን በቀልን ወዳጅ አድርግያለሁ
ነፍሴ ተጎሳቁላ ፍጹም ሳያምርባት
ተኮንና እንዳትኖር ይቅርታን አስተምራት
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ