ኢየሩሳሌም
Yerusalem
2010 · 5:24 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ኢየሩሳሌም ቅድስቲት ከተማ
የጐዳናሽ ውጥንቅጡ ቢበዛ እንኳ
ሳላይሽ አልቀርም በአምላክ ኃይል እርዳታ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
የናፈቀኝ ዜማ የቅዱስ ዝማሬ (፪x)
አልቀርም ሳልዘምር ከጻድቃን አብሬ
ከበጉ ዙፋን ሥር ሳልዞር በደስታ (፪x)
አልቀርም ሳላይሽ አንቺ ቅዱስ ቦታ
ማቋረጫው መንገድ ሊጠልፈኝ ቢነሳ (፪x)
ሳላየው አልቀርም የይሁዳን አንበሳ
ብቻዬን ብቀርም መንገደኛው ሸሽቶ (፪x)
ሳላየው አልቀርም ኢየሱሴ መጥቶ
የመናኝ ተራራን መቧጠጥ ቢያቅተኝ (፪x)
የበረሃው ጉዞ ውኃ ጥም ቢጐዳኝ
የሚያረካው ጌታ ሲመጣ ከሰማይ (፪x)
ይረዳኛል በርግጥ ያቺን ቦታ እንዳይ
አዝማች · Chorus
ኢየሩሳሌም ቅድስቲት ከተማ
የጐዳናሽ ውጥንቅጡ ቢበዛ እንኳ
ሳላይሽ አልቀርም በአምላክ ኃይል እርዳታ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም አዲስ ሕይወት
በድል ዳግም የምናይሽ የምንወርስሽ መቼ ይሆን
አይቀር ቁርጥ ነው (፫x)
ማረፊያችን እፎይታችን ስንወርስሽ ነው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ