Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

በመስቀል የሞተው

Track 1 Adane Asnake Mamo

2014 · ትራክ 1 · 5:28 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በመስቀል የሞተው ኢየሱስ ያድናል/4

ያድናል ኢየሱስ ያድናል/4

ስለ ሐጥአትህ በሰው ልጅ ተገፍቶ

የሕማም ሰው ሆኖ በጦርም ተወግቶ

የእኔን የአንተን ደዌ በመስቀል የሻረው

ኢየሱስ ክርስቶስ ብቸኛ አዳኝ ነው

አዳኝ ማንም የለም ኢየሱስ ብቻ ነው/4

ከወርቅ እና ዕንቁ ቢሰራ ከብረት

ግዑዝ አያድንም አይሆንህም ሕይወት

በመስቀል ተዋርዶ ስላንተ የሞተው

ሁልጊዜ ተመልከት አዳኝህ እርሱ ነው

አዳኝ ማንም የለም ኢየሱስ ብቻ ነው/4

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ