Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ምህረቱ በቤቱ

Track 12 Adane Asnake Mamo

2014 · ትራክ 12 · 6:11 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ምሕረቱ በቤቱ አኑሮኛል

ርህራሔው ከሃጥያት ጠብቆኛል

በሃጥያት የሚሸነፍ ይህንን ስጋ ለብሼ

በክፋት የሚነዳ ማንነት ይዤ

እንዳሸንፍ ሃጥያትን እንድገዛው ስግዬን

ሰጥቶኛል ሕያው የሆነ መንፈሱን

በማሕጸን ሥሰራ አጥንቶቼም ሲገጥም

ለራሱ ክብር መገለጫ እንድሆን

አስቀድሞ መረጠኝ አስቦ ነው የወለደኝ

ቃሉን እየመገበ አሳደገኝ

እየሱስ እረኛዬ በፍቅር የሚመራኝ

በራሱ ዋጋ ገዝቷታል ላይተወኝ

በለምለም መስክ አድራለሁ

በቅፉ እሆናለሁ

እሱ ካለኝ በሰላም እኖራለሁ

https://www.youtube.com/watch?v=vZi2LflQ8WM&list=PLvd6Ao9nWjlx8WI8reelS1yPGnyP_KgtX&index=12

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ