ጸሎቴን ይሰማል
Tselotien Yesemal
ትራክ 1 · 5:46 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የሰማያት ዳርቻ ሰሪ
የምድርም ሁሉ ፈጣሪ
አንተ አይደለህም ወይ
እግዚአብሔር ኤልሻዳይ
ኧረ አንተ አይደለህም ወይ
እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ
አላቋርጥ ማንኳኳቴን እስኪከፈትልኝ ደጁ
ፀሎቴንም እስኪሰማ እስኪዘረጋላኝ እጁ
ዘንበል እስኪል ከዙፋኑ እስኪበዛልኝ ምሕረቱ
ዝም አልልም አላቆምም መፈለጌን ማየት ፊቱን
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር በዙፋኑ ያለው
ፀሎቴን ይሰማል አውቃልሁ
አምላኬ በማደሪያው ያለው
ይራራል ይምራል አምናለሁ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እስኪለወጥ በምስጋና የለቅሶ የእንባ ጩኸቴ
ሙሉ ሆኖ እንኪመጣ እስኪለቀቅ በረከቴ
ከአንደበቱ እስኪወጣ የበረከት ንግግር
አልነሳም ዞር አልልም ከዙፋኑ ከእግሩ ስር
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር በዙፋኑ ያለው
ፀሎቴን ይሰማል አውቃልሁ
አምላኬ በማደሪያው ያለው
ይራራል ይምራል አምናለሁ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የተስፋውን ቃል አስቦ ሊፈጽመው እስኪነሣ
የምድሬኔም ኃጢአት በደል ይቅር ብሎ እስኪረሳ
ክብሩን ዳግም እስኪመልስ በቅዱሱ ማደሪያው
አላቆምም ክርክሬን እስኪነሣ ከስፍራው
ቁጥር 4 · Verse 4
የሚሰማ የሚመልስ የሚምር ነው የሚራራ (፪x)
በጎነቱ እጅግ ብዙ በሞገሱ የተፈራ (፪x)
ቸር እንደእርሱ ስለሌለ በምድር ቢሆን በሰማይ (፪x)
አንዲቷም ቀን አታልፍብኝ ያምላኬን ፊቱን ሳላይ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ