እርሱ ይላቅ እንጂ
Ersu Ylaq Enji
5:41 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ሊልቅ የሚገባው እርሱ ይላቅ እንጂ
እኔ ዝቅ ልበል እኔ ዝቅ ልበል ዝቅ ልበል እንጂ
ከፍታዉን ሁሉ የክብሩን ቦታ
እሰዋለታለው ለትልቁ ጌታ
ክብር ክብር ክብር ለእግዚአብሔር
ሞገስ ሞገስ ሞገስ ለኢየሱስ
መክበር መክበር መክበር ለእግዚአብሔር
መንገስ መንገስ መንገስ ለጌታ መንፈስ ቅዱስ
ቁጥር 1 · Verse 1
ከሰማይ የመጣው ከሁሉ በላይ ከሁሉ በላይ
በሁሉ ላይ ጌታ ደግሞም ኤልሻዳይ ደግሞም ኤልሻዳይ
ጉልበት ሁሉ ለእርሱ ለርሱ ይሰግዱለታል ለርሱ ይሰግዱለታል
ፍጥረት በራሱ ላይ አንግሶ ሾሞታል አንግሶ ሾሞታል
በከፍታዎች ላይ ከፍ ያለ ከፍ ያለ
እንደእርሱ በሞገስ ማን አለ ማን አለ ማን አለ
በከፍታዎች ላይ ከፍ ያለ ከፍ ያለ
እንደእርሱ በውበት ማን አለ ማን አለ ማን አለ
አዝማች · Chorus
ሊልቅ የሚገባው እርሱ ይላቅ እንጂ
እኔ ዝቅ ልበል እኔ ዝቅ ልበል ዝቅ ልበል እንጂ
ከፍታዉን ሁሉ የክብሩን ቦታ
እሰዋለታለው ለትልቁ ጌታ
ክብር ክብር ክብር ለእግዚአብሔር
ሞገስ ሞገስ ሞገስ ለኢየሱስ
መክበር መክበር መክበር ለእግዚአብሔር
መንገስ መንገስ መንገስ ለጌታ መንፈስ ቅዱስ
ቁጥር 2 · Verse 2
ምድርና ሞላዋ ለርሱ ለእግዚአብሔር ናት ለርሱ ለእግዚአብሔር ናት
አለምም የቃሉ ትዕዛዝ ስራ ናት ትዕዛዝ ስራ ናት
ሁሉ በእርሱ ለእርሱ ተፈጥረዋልና ተፈጥረዋልና
ለታላቅነቱ ይብዛለት ምስጋና ይብዛለት ምስጋና
በከፍታዎች ላይ ከፍ ያለ ከፍ ያለ
እንደእርሱ በሞገስ ማን አለ ማን አለ ማን አለ
በከፍታዎች ላይ ከፍ ያለ ከፍ ያለ
እንደእርሱ በውበት ማን አለ ማን አለ ማን አለ
ቁጥር 3 · Verse 3
አልሰለችም ከፍቶ ዝም አልልም
ጌታን ከማመስገን ወደኋላ አልልም ወደኋላ አልልም ወደኋላ አልልም
አምላኬን ከማምለክ እኔ ዝም አልልም እኔ ዝም አልልም
አልሰለችም ከፍቶ ዝም አልልም
ጌታን ከማመስገን ወደኋላ አልልም ወደኋላ አልልም ወደኋላ አልልም
አምላኬን ከማምለክ እኔ ዝም አልልም
ቁጥር 4 · Verse 4
አይጓደልበት አምልኮ አይጓደልበት ምስጋና ለዚህ ለገናና
አይጓደልበት ዝማሬ አይጓደልበት እልልታ ለሚወደን ጌታ
አይጓደልበት አምልኮ አይጓደልበት ምስጋና ለዚህ ለገናና
አይጓደልበት ዝማሬ አይጓደልበት እልልታ ለሚወደን ጌታ
በእርግጥ አምላክ ነዉ የጌቶች ጌታ የጌቶች ጌታ
ደሞ ሚገባው ዝማሬ እልልታ ዝማሬ እልልታ
በእርግጥ አምላክ ነዉ ኃያል ገናና ኃያል ገናና
ደሞ ሚገባው ክብር ምስጋና ክብር ምስጋና
የሚገባው ነው ክብር ምስጋና(5)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ