ይችላል
Yechelal
ትራክ 2 · 5:59 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ሳልጠራጠር ሁሉን ቻይነቱን
አመልከዋለሁ እያየሁ ጉልበቱን/ሞገሱን
ሳልጠራጠር ሁሉን ቻይነቱን
አመልከዋለሁ እያየሁ ብርታቱን/ችሎቱን (፪x)
የእኔ/የእኛ ጌታ ሁሉንም ይችላል
እስኪ የቱ ምንስ አቅቶታል
የእኔ/የእኛ ጌታ ሁሉንም ይችላል
ኧረ የቱ ምንስ አቅቶታል (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ግዙፉን ተራራ ማደላደል ነው ዎይ
(እግዚአብሔር ይህንን ይችላል)
ጥልቁን ሸለቆ ውሃ መሙላት ነው ዎይ
(እግዚአብሔር ይህንን ይችላል)
የተዘጋውን ደጅ መከፋፈት ነው ዎይ
(እግዚአብሔር ይህንን ይችላል)
ለጨለመው ሕይወት ብርሃን መስጠት ነው ዎይ
(እግዚአብሔር ይህንን ይችላል)
ይችላል ይችላል ፥ ይችላል እርሱ ይችላል
ይችላል ይችላል ፥ ይችላል ጌታ ይችላል
ይችላል ይችላል ፥ ይችላል በደንብ ይችላል
ይችላል ይችላል ፥ ይችላል ጌታ ይችላል
ቁጥር 2 · Verse 2
አንሱ ካለ ማንሳት እንጂ ድንጋዩን
መከራከር መሟገቱ ለምን
ሕያው ይሁን ይፈታ እንጂ አልዓዛር
ከሰው እኩል ይቁም ይብቃ ለክብር
ሁሉን ቻዩ ተናገረ ቃል አወጣ
እስከመቼ ያለማመን ብሎ ጣጣ
የማይሆነውን የሚያደርግ እንዲሆን
ያለረዳት ያለአጋዥ ብቻውን
ክብር ሁሉ ለእርሱ ብቻ ለእግዚአብሔር (፫x)
አዝማች · Chorus
ሳልጠራጠር ሁሉን ቻይነቱን
አመልከዋለሁ እያየሁ ጉልበቱን/ሞገሱን
ሳልጠራጠር ሁሉን ቻይነቱን
አመልከዋለሁ እያየሁ ብርታቱን/ችሎቱን (፪x)
የእኔ/የእኛ ጌታ ሁሉንም ይችላል
እስኪ የቱ ምንስ አቅቶታል
የእኔ/የእኛ ጌታ ሁሉንም ይችላል
ኧረ የቱ ምንስ አቅቶታል (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የሞተውን ተነስ ውጣ ማለት ነው ዎይ
(እግዚአብሔር ይህንን ይችላል)
የታሰረውን ሰው ፈትቶ መልቀቅ ነው ዎይ
(እግዚአብሔር ይህንን ይችላል)
እንቆቅልሽ ፍቺ መልስ መስጠት ነው ዎይ
(እግዚአብሔር ይህንን ይችላል)
የጠላትን ሃሳብ ማፈራረስ ነው ዎይ
(እግዚአብሔር ይህንን ይችላል)
ይችላል ይችላል ፥ ይችላል እርሱ ይችላል
ይችላል ይችላል ፥ ይችላል ጌታ ይችላል
ይችላል ይችላል ፥ ይችላል በደንብ ይችላል
ይችላል ይችላል ፥ ይችላል ጌታ ይችላል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ