ላመሰግንህ እድል ስላገኘሁ
Lamesegeneh Edel Selagengehu
6:22 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ከኖርኩበት ከዚያ ከሞት ሰፈር
አስኮብልሎኝ ድንቁ ያንተ ፍቅር
እርግፍ አርጎ ሁሉን አስጣለና
አዲስ ህይወት ጎዳና
ኦ ድንቅ ነው መኖር ካንተ ጋራ
በሸለቆ ቢሆን በተራራ
ላመስግንህ እጆቼን አንስቼ
ከጠላቴ ወጥመድ ሁሉ አምልጬ
አዝማች · Chorus
(ላመሰግንህ እድል ስላገኘሁ
በዜማ ቃሌ አፌን እከፍታለሁ
ከፍ ላድርግህ መቅደስ ህ ልግባና
ባዲስ ዝማሬ ባዲሱ ምስጋና) x2
ተመስገን ዛሬም ተመስገን
ተመስገን ነገም ተመስገን
ተመስገን ሁሌም ተመስገን
ተመስገን ዘወትር ተመስገን
ቁጥር 2 · Verse 2
እሃሃሃ በእውነት እንደዳነ
አሃሃሃ በሕይወት እንዳለ ሰው
አሃሃሃ እስቲ በጐነትህን
አሃሃሃ እኔም ልዘምረው x2
አሃሃሃ ለሰው ሁሉ ልንገር
አሃሃሃ ማዳንህን ላውራ
አሃሃሃ ሁሌ በብርሃን
አሃሃሃ ቆሜ በተራራ x2
አዝማች · Chorus
(ላመሰግንህ እድል ስላገኘሁ
በዜማ ቃሌ አፌን እከፍታለሁ
ከፍ ላድርግህ መቅደስ ህ ልግባና
ባዲስ ዝማሬ ባዲሱ ምስጋና) x2
ተመስገን ዛሬም ተመስገን
ተመስገን ነገም ተመስገን
ተመስገን ሁሌም ተመስገን
ተመስገን ዘወትር ተመስገን
ቁጥር 3 · Verse 3
ድንቁ ፍቅርህ ካደናኝ በኋላ
በሕይወቴ ክቡር ጸጋን ሞላ
በመንግሥትህ እንድል ደፋ ቀና
ወግ ደረሰኝ እኔም ታሰብኩና
ቸርነትህ ኸረ እንደምን በዛ
ዝቅ ልበል ለክብርህ ልገዛ
በዝማሬ በብዙ ምሥጋና
ላሞጋግስህ ላድርግህ ገናና
አዝማች · Chorus
(ላመሰግንህ እድል ስላገኘሁ
በዜማ ቃሌ አፌን እከፍታለሁ
ከፍ ላድርግህ መቅደስ ህ ልግባና
ባዲስ ዝማሬ ባዲሱ ምስጋና) x2
ተመስገን ዛሬም ተመስገን
ተመስገን ነገም ተመስገን
ተመስገን ሁሌም ተመስገን
ተመስገን ዘወትር ተመስገን
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ