አቤቱ በህዝብህ ሞገስ አስበን
Abietu Behezbeh Moges Aseben
2006 · ትራክ 9 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አቤቱ በህዝብህ ሞገስ አስበን
በመድሃኒትህም ጐብኘን
ህዝብህ ለአርባ አመታት ሲጓዝ ምድረ በዳ
ሞገስ ስለሆንከው ከቶ ሳይጐዳ
እያዘነብክለት ከሰማያት መና
ስትጠብቅ ስትመራው በእሳት በደመና
ሞገስህን አግኝቶ ህዝብህም በርትቶ
ድል በድል አድርጓል ጠላቶቹን ረግጦ
ህዝብህን ባሰብክበት ሞገስህ አስበን
ማምለጥ እንድንችን ከከበበን ነገር
አዝማች · Chorus
በህዝብህ ሞገስ አስበን (፬x)
በህዝብህ ሞገስ አስበን (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ያየ የጋለው ፍቅርህ የቀድሞው ሕይወታችን
ዛሬ ቀስሞብናል ቀዝቅዟል ልባችን
አንድነት ሲጠፋ መለያየት በዝቶ
ስም ብቻ ሆነናል ሕይወታችን ሞቶ
ዛሬ ግን ጌታ ሆይ ጐብኘን በ???
ባሰብክበት ምህረት ልክ እንደህዝቦችህ
እጆቿን ወደ አንተ ኢትዮጵያም ትዘርጋ
ጊዜው አሁን ይሁን ሞገስህ ይብዛና
አዝማች · Chorus
በህዝብህ ሞገስ አስበን (፬x)
በህዝብህ ሞገስ አስበን (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በአንደበት ፍቅር የለበጥ አንድነት
ቤትህን አረግነው ተንኮል የሞላበት
በአፋችን ሌላ በልባችን ሌላ
የያዝነውን እምነት አረግነው ደካማ
መግባባት ይኑረን ቃላችን አንድ ይሁን
እንደተናገርነው እንዲሁ እንድንኖር
ዛሬ ለውጥን ስጠን ጌታ ለሁላችን
በሞገስህ አስበን ይቀየር ልባችን
አዝማች · Chorus
በህዝብህ ሞገስ አስበን (፬x)
በህዝብህ ሞገስ አስበን (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ