Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አቤቱ መተላለፌን ደምስሳት

Abietu Metelalefien Demsesat

2006 · ትራክ 2 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

"አምላክ ሆይ ስለዘለዓለማዊ ፍቅርህ ይቅር በለኝ

ስለታላቁ ምህረትህም ኀጢአቴን ደምስስልኝ

በደለኔን ሁሉ አጥበህ አስወግድልኝ

ከኀጢአቴም አንጻኝ

እኔ ስህተቴን አውቃለሁ የኀጢአቴንም ብዛት ዘወትር እገነአባለሁ

እኔ ያመጽኹት በአንተ ላይ ነው

የበደልኹትም አንተን ብቻ ነው

አንተ የምትጠላውን ነገር አደረግኩ

ስለእዚህ በእኔ ላይ መፍረድህና እኔንም መቅጣትህ ትክክል ነው

ኀጢአተኛ ሆኜ እንደተወለድኩ ታውቃለህ

ከተጸነስኩበት ጊዜም ጀምሮ ኀጢአተኛ ነኝ

አንተ ቅንነትን እና እውነትን ስለምትወድ

የጥበብህን ሚስጥር አስተምረኝ

በህጾብ ቅጠል ረጭተህ ኀጢአቴን አስወግድልኝ እኔም እነጻለሁ

እጠበኝ እኔም ከበረዶ ይበልጥ ነጭ እሆናለሁ

የደስታንና የሃሴትን ድምጽ አሰማኝ

ምንም እንኳን ሰብረህ ያደቀከኝ ብሆንም

እንደገና ደስ አሰኘኝ

ኀጢአቴን አትቁጠርብኝ ከበደሌም አንጻኝ

አምላኬ ሆይ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ

አዲስና ታማኝ ሆኖ የሚጸና መንፈስ በውስጤ አኑርልኝ

ከፊትህ አታርቀኝ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ አትውሰድብኝ

ከአዳኝነትህ የሚመነጨውን ደስታ መልሰህ ስጠኝ

እንድታዘዝም ፈቃደኛ አድርገኝ"

አቤቱ እንደቸርነትህ ብዛት

እንደ ምህረትህ ብዛት

መተላለፌን ደምስሳት (፬x)

እኔ መተላለፌን አውቃለሁ

ከቶ አልክድም ፊትህ

በደሌም ሁልጊዜ በፊትህ ነው

አንሳኝ በምህረትህ

እንድትመራኝ ብዬ መጣሁ

እጠበኝ ከበረዶ ይልቅ ነጭ እሆናለሁ (፪x)

አቤቱ እንደቸርነትህ ብዛት

እንደ ምህረትህ ብዛት

መተላለፌን ደምስሳት (፬x)

ለበደሌ ክርክር አላቀርብም

እኔ አልሟገትም

መናዘዝ እንጂ እያልኩኝ ኀጢአተኛ ነኝ

ሌላ ምን ምርጫ አለኝ

ስለዚህ በሂሶብ??? እርጨኝና

እጠበኝ ከበረዶ ይልቅ ነጭ እሆናለሁ (፪x)

አቤቱ እንደቸርነትህ ብዛት

እንደ ምህረትህ ብዛት

መተላለፌን ደምስሳት (፪x)

"ጌታ ሆይ ቅዱስ መንፈስህ ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ"

ቅዱስ መንፈስህን (፪x)

ከእኔ ላይ (፪x)

ኧረ አትውሰድብኝ (፪x)

ቅዱስ መንፈስህን (፪x)

ከእኔ ላይ (፪x)

ኧረ አትውሰድብኝ (፪x)

ታድያ እኔ ማነኝ ይህን ታላቅ ስም ልጠራ

ታዲያ እኔ ማነኝ ፊትህ ለማቅረብ ምሥጋና

ግን ፊትህ ለመቆም ሞገስ/ምህረት ከአገኘሁ

ምሥጋናን ምሥጋና ምሥጋናን እሰዋለሁ

ምሥጋናን ምሥጋና ምሥጋናን እሰዋለሁ (፪x)

ምሥጋና ምሥጋና ለኢየሱስ ምሥጋና

ይገባሃል አምላክ ለአንተ

ለሆንከው ገናና (፪x)

"እግዚአብሔር መሃሪና ይቅር ባይ ነው

ከቁጣ የራቀ ምህረቱም የበዛ

ሁልጊዜ አይቀስፍም ለዘለዓለምም አይቆጣ

እንደኀጢአታችን አላደረገብንም እንደበደላችንም አልከፈለንም

ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል እንዲሁ እግዚአብሔር

ምህረቱን በሚፈሩት ላይ አጠነከረ

ቸር እንደሆነ ምህረቱ ለዘለዓለም እንደሆነች

እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሁሉ አሁን ይናገሩ"

ምህረቱ ለዘለዓለም ነው (፬x) ፣ ምህረቱ ለዘለዓለም ነው (፬x)

ምህረቱ ለዘለዓለም ነው (፬x) ፣ ምህረቱ ለዘለዓለም ነው (፬x)

ምህረቱ ለዘለዓለም ነው (፬x) ፣ ምህረቱ ለዘለዓለም ነው (፬x)

ምህረቱ ለዘለዓለም ነው (፬x) ፣ ምህረቱ ለዘለዓለም ነው (፬x)

ምህረቱ ለዘለዓለም ነው (፬x) ፣ ምህረቱ ለዘለዓለም ነው (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ