ማሳዘን አልፈልግም አንተን
Masazen Alfelegem Anten
2006 · ትራክ 3 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ማሳዘን አልፈልግም አንተን (፪x)
ማስቀየም አልፈልግም አንተን (፪x)
ላሳዝንህ አልፈልግም አንተን (፪x)
ላስቀይምህ አልፈልግም አንተን (፪x)
ብዙ ውለታ አለብኝ
ያደረከው ለሕይወቴ ለቤቴ ለኑሮዬ (፪x)
ማሳዘን አልፈልግም አንተን (፪x)
ማስቀየም አልፈልግም አንተን (፪x)
ብዙ ውለታ አለብኝ
ያደረከው ለሕይወቴ ለቤቴ ለኑሮዬ (፪x)
የሞላኸው አለ ጐድሎብኝ
የጠገንከውም አለ ተሰብሮብኝ
የአደስክልኝ ብዙ ነው አርጅቶብኝ
የመለስከውም አለ ግራ ገብቶኝ
ይሄ ሁሉ በዝቶልኝ ላሳዝንህ አልፈልግም ይከብደኛል
ሌላው ቢቀር ዘመኖቼ ይመሰክሩልኛል
ሌላው ቢቀር ዕድሜዬ ይመሰክርልኛል
አዝማች · Chorus
ማሳዘን አልፈልግም አንተን (፪x)
ማስቀየም አልፈልግም አንተን (፪x)
ላሳዝንህ አልፈልግም አንተን (፪x)
ላስቀይምህ አልፈልግም አንተን (፪x)
ብዙ ውለታ አለብኝ
ያደረከው ለሕይወቴ ለቤቴ ለኑሮዬ (፪x)
ማሳዘን አልፈልግም አንተን (፪x)
ማስቀየም አልፈልግም አንተን (፪x)
ብዙ ውለታ አለብኝ
ያደረከው ለሕይወቴ ለቤቴ ለኑሮዬ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ለሃዘን ቀን ለደስታ ቀን
ለፍርድ ቀን ለምጽዓት ቀን
የታተምኩበት የአንተ ማኅተም
የእርስቴ መያዣ ምጽናናበት
ኀጢአትን ባደርግ የምወቀስበት
ስለሰማዩ ሚስጥር የምረዳበት
መንፈስ ቅዱስ እርሱ ነው ምጽናናበት
የቀረ ይቀራል እንጂ (፫x)
አሳዝኜው አልወጣም/አልርቅም ከእርሱ እጅ (፬x)
አዝማች · Chorus
ማሳዘን አልፈልግም አንተን (፪x)
ማስቀየም አልፈልግም አንተን (፪x)
ላሳዝንህ አልፈልግም አንተን (፪x)
ላስቀይምህ አልፈልግም አንተን (፪x)
ብዙ ውለታ አለብኝ
ያደረከው ለሕይወቴ ለቤቴ ለኑሮዬ (፪x)
ማሳዘን አልፈልግም አንተን (፪x)
ማስቀየም አልፈልግም አንተን (፪x)
ብዙ ውለታ አለብኝ
ያደረከው ለሕይወቴ ለቤቴ ለኑሮዬ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ