Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እስቲ ልለምነው ጌታዬን

Esti Lelemenew Gietayien

2006 · ትራክ 6 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ስለዚህ ወደ እግዚአብሔር ልመና

ጸሎት ምልጃና ምሥጋና

ለሰዎች ሁሉ እንዲደረግ ከሁሉም በፊት እመክራለሁ

በመንፈሳዊነትና በመልካም ጠባይ እየተመራን

በሰላምና በጸጥታ እንድንኖር በተለይ

ለነገሥታትና በስልጣን ላይ ላሉ ሁሉ ጸልዩ

እስቲ ልለምነው ጌታዬን ስለአገሬ ስለህዝቤ

የራሴን የግሌን ነገር ትቼ

እስቲ ልለምነው ጌታዬን ስለአገሬ ስለምድሬ

የራሴን የጸሎት ርዕስ ትቼ

ለሹማምንት ለገዢዎች ለአለቆች

ፊቱ ልቅረብ ልጸልይ ተግቼ ስለሌሎች

ለሹማምንት ለገዢዎች ለአለቆች

ፊቱ ልቅረብ ልጸልይ ተግቼ ስለሌሎች (፪x)

የአገሬ መፍትሄዋ የእንቆቅልሿ መፍቻዋ

ቁልፉ ያለው ሰው ጋር አይደል

ታዲያ ማንም አይታለል

ስለእልቂቷ ወሬን ትቼ ስንበረከክ ተደፍቼ

ይሰማኛል አምነዋለሁ ከዚም በፊት አይቻለሁ

ሁሉም ነገር ያበጀዋል ዝብርቅርቁን ያሳምራል

እስቲ ልለምነው ጌታዬን ስለአገሬ ስለህዝቤ

የራሴን የግሌን ነገር ትቼ

እስቲ ልለምነው ጌታዬን ስለአገሬ ስለምድሬ

የራሴን የጸሎት ርዕስ ትቼ

ለሹማምንት ለገዢዎች ለአለቆች

ፊቱ ልቅረብ ልጸልይ ተግቼ ስለሌሎች

ለሹማምንት ለገዢዎች ለአለቆች

ፊቱ ልቅረብ ልጸልይ ተግቼ ስለሌሎች (፪x)

በችግሯ ከምሳለቅ ይልቅ እኔ ፊቱ ልውደቅ

ባለምነው ባልጠይቀው እዳው በእኔ ጫና ላይ ነው

መፍትሄ ላይሆን ወሬን ትቼ ልንበረከክ ፊቱን ሽቼ

ሰሚ አምላክ እያመንኩኝ ለምን መፍትሄ አጣለሁኝ

ትልቅም ለውጥ አመጣለሁ ለምድሬም ፈውስ እሆናለሁ

እስቲ ልለምነው ጌታዬን ስለአገሬ ስለህዝቤ

የራሴን የግሌን ነገር ትቼ

እስቲ ልለምነው ጌታዬን ስለአገሬ ስለምድሬ

የራሴን የጸሎት ርዕስ ትቼ

ለሹማምንት ለገዢዎች ለአለቆች

ፊቱ ልቅረብ ልጸልይ ተግቼ ስለሌሎች

ለሹማምንት ለገዢዎች ለአለቆች

ፊቱ ልቅረብ ልጸልይ ተግቼ ስለሌሎች (፪x)

ብለምነው ስለአገሬ ሸክም ቢኖረኝ ለምድሬ

ያለባትን ችግር ሁሉ ይዤ ብቀርብ ከመስቀሉ

ጌታዬ እኮ ያደምጠኛል እንደሃሳቡ ይመልሳል

ሳልታክት ፊቱ እቀርባለሁ ቃሉም ይላል ጸልያለሁ

ሸክሟን ሳሳየው የምድሬን ይፈውሳታል አገሬን

እስቲ ልለምነው ጌታዬን ስለአገሬ ስለህዝቤ

የራሴን የግሌን ነገር ትቼ

እስቲ ልለምነው ጌታዬን ስለአገሬ ስለምድሬ

የራሴን የጸሎት ርዕስ ትቼ

ለሹማምንት ለገዢዎች ለአለቆች

ፊቱ ልቅረብ ልጸልይ ተግቼ ስለሌሎች

ለሹማምንት ለገዢዎች ለአለቆች

ፊቱ ልቅረብ ልጸልይ ተግቼ ስለሌሎች (፪x)

ኢትዮጵያን ግብኛት ተመልከታት

በቃልኪዳንህ አስባት (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ