Agegnehu Yideg/Haylegna Endante Yelem/Weletaw
1992 · ትራክ 12 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ውለታው (፫x) ውለታው በዛብኝ
እግዚአብሔር አምላኬ ድንቅ አደረገልኝ
ውለታው በዛብኝ
ውለታው (፫x) ውለታው በዛብኝ
ናዝራዊው ወዳጄ ብዙ አደረገልኝ
ውለታው በዛብኝ
ቁጥር 1 · Verse 1
ኢየሱሴ ለእኔ በመስቀል ሞተልኝ
ውለታው በዛብኝ
በእንጨት ተንጠልጥሎ እርግማን ሆነልኝ ውለታው በዛብኝ
በከበረ ደሙ በውድ ዋጋ ገዛኝ
ውለታው በዛብኝ
ሲጠራኝ ብቻዬን ዛሬ ግን አበዛኝ
ውለታው በዛብኝ
ከአዕምሮ በላይ ነው የእርሱ ውለታ
እንዴት ላመስግነው ይህንን ጌታ
እጅግ ብዙ ነው የእርሱ ውለታ
እንዴት ላመስግነው ይህንን ጌታ
አዝማች · Chorus
ውለታው (፫x) ውለታው በዛብኝ
እግዚአብሔር አምላኬ ድንቅ አደረገልኝ
ውለታው በዛብኝ
ውለታው (፫x) ውለታው በዛብኝ
ናዝራዊው ወዳጄ ብዙ አደረገልኝ
ውለታው በዛብኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
ከበለስ ዛፍ በታች ተቀምጬ አይኝ
ውለታው በዛብኝ
ተንኮል የሌለብህ የእስራኤል ልጅ አለኝ
ውለታው በዛብኝ
ታማኝ አድርጐ ቆጥሮ ለአገልግሎት ሾመኝ ውለታው በዛብኝ
ኢየሱሴን መጠጋት ለእኔ እጅግ ጠቀመኝ
ውለታው በዛብኝ
ከአዕምሮ በላይ ነው የእርሱ ውለታ
እንዴት ላመስግነው ይህንን ጌታ
እጅግ ብዙ ነው የእርሱ ውለታ
እንዴት ላመስግነው ይህንን ጌታ
አዝማች · Chorus
ውለታው (፫x) (ውለታው በዛብኝ)
እግዚአብሔር አምላኬ ድንቅ አደረገልኝ
ውለታው በዛብኝ
ውለታው (፫x) ውለታው በዛብኝ
ናዝራዊው ወዳጄ ብዙ አደረገልኝ
ውለታው በዛብኝ
ቁጥር 3 · Verse 3
በግ እረኛ ነብረኩ ገና ብላቴና
ውለታው በዛብኝ
እግዚአብሔር ፊት ሞገስ አገኘሁኝና
ውለታው በዛብኝ
እኔን በናቁኝ ፊት ራሴን በዘይት ቀባኝ
ውለታው በዛብኝ
ንጉሡ ሊያከብረኝ ወደ እልፊኙ አገባኝ
ውለታው በዛብኝ
ሰው ላደረገልኝ እንደዚህ ዛሬ
ሥሙን ላወድሰው በዝማሬ
እጅግ ብዙ ነው የእርሱ ውለታ
እንዴት ላመስግነው ይህንን ጌታ (7)
አዝማች · Chorus
ውለታው (፫x) (ውለታው በዛብኝ)
እግዚአብሔር አምላኬ ድንቅ አደረገልኝ
ውለታው በዛብኝ
ውለታው (፫x) ውለታው በዛብኝ
ናዝራዊው ወዳጄ ብዙ አደረገልኝ
ውለታው በዛብኝ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ