Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ርዕስ

Title

1992 · ትራክ 6 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ባለፈው ዘመኔስ ብዙ አጥፍቻለው

ባለማስተዋሌም ተጎድቻለው

ፍቅርን የተሞላህ ባታግዘኝ ኖሮ

እንዴት ይዘለቃል የዚህ ምድር ኑሮ

አሁንም ጌታዬ መንገዴን አደራ

ታዳጊ አንተ ነህ በሚገጥመኝ መከራ (2)

መንገዴን አደራ አደራ

በቀረው ዘመኔስ ስራህን ስራ (2)

ጉዞዬ ከብዶብኝ ስወድቅ ስነሳ

እዚህ ደርሻለው በብዙ አበሳ

የቀረው ዘመኔስ ብሩህ ይሁንልኝ

ኢየሱሴ በኃይልህ ስራዬን ስራልኝ

የኋላዬን ልርሳ ወዳንተ ልጠጋ

ከፊቴ ያለውን ለመያዝ ልዘርጋ

መንገዴን አደራ አደራ

በቀረው ጉዞዬስ ስራህን ስራ(2)

በስጋዬ ምኞት በከንቱ ስገዛ

ስንት ጊዜ አቃጠልኩ እንዲሁ በዋዛ

ለቅዱሱ አደራህ ታማኝ አልነበርኩም

እንደልብህ ደስታም አላገለገልኩም

እንግዲህስ ጌታ ስራብኝ እንደሰው

(በጭንጋፉ) በትንሹ ባሪያ ከሁሉም በማንሰው

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ