አቤት የእግዚአብሔር አሰራሩ
Abiet Yegziabhier Aseraru
1992 · ትራክ 2 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
"አቤት የእግዚአብሔር አሰራሩ አሰራሩ"
አቤት የእግዚአብሔር (፪x)የእግዚአብሔርስ አሰራሩ
ፍፁም ነው አይሳሳትም የእኛስ አምላክ ግሩም ነው በምክሩ
አቤት የእግዚአብሔር (፪x)የእግዚአብሔርስ አሰራሩ
ፍፁም ነው አይሳሳትም የእኛስ አምላክ ግሩም ነው በምክሩ
ቁጥር 1 · Verse 1
መካኒቱ ሰባት ወለደች
ብዙ የወለደችውም ደከመች
አቤት የእግዚአብሔር (፪x)የእግዚአብሔርስ አሰራሩ
ፍፁም ነው አይሳሳትም የእኛስ አምላክ ግሩም ነው በምክሩ
ቁጥር 2 · Verse 2
ከአሳዳጆች ዋና የነበረ
የሳዖል ደንዳና ልብ ተሰበረ
አቤት የእግዚአብሔር (፪x)የእግዚአብሔርስ አሰራሩ
ፍፁም ነው አይሳሳትም የእኛስ አምላክ ግሩም ነው በምክሩ
ቁጥር 3 · Verse 3
ናቡከደነጾር ሲኩራራ
ሰባት ዘመን እንደ ከብት ሣር በላ
አቤት የእግዚአብሔርስ የአምላካችን የአባታችን አሰራሩ
ፍፁም ነው አይሳሳትም የእኛስ አምላክ ግሩም ነው በምክሩ
ቁጥር 4 · Verse 4
ዮሴፍ የተሸጠ ለባርነት
ዘመኑን ጠብቆ አገኘ ሹመት
አቤት የእግዚአብሔር (፪x)የእግዚአብሔርስ አሰራሩ
ፍፁም ነው አይሳሳትም የእኛስ አምላክ ግሩም ነው በምክሩ
ቁጥር 5 · Verse 5
አልቆለታል ተብሎ የተዘጋ
መልስ ተገኘለት ሌሊቱ ነጋ
አቤት የእግዚአብሔር (፪x) የእግዚአብሔርስ አሰራሩ
ፍፁም ነው አይሳሳትም የእኛስ አምላክ ግሩም ነው በምክሩ
ቁጥር 6 · Verse 6
ሲከሰን ሲያስጨንቀን የነበረ
እግዚአብሔር አሰበን ሰይጣን አፈረ
አቤት የእግዚአብሔር የአምላካችን የአባታችን አሰራሩ
ፍፁም ነው አይሳሳትም የእኛስ አምላክ ግሩም ነው በምክሩ
ቁጥር 7 · Verse 7
አጥንቶች ተበታትነው የነበሩ
ለእርሱ ምን ይሳናል ነፍስ ዘሩ
አቤት የእግዚአብሔር (፪x) የእግዚአብሔርስ አሰራሩ
ፍፁም ነው አይሳሳትም የእኛስ አምላክ ግሩም ነው በምክሩ
አዝማች · Chorus
አቤት የእግዚአብሔር (፪x) የእግዚአብሔርስ አሰራሩ
ፍፁም ነው አይሳሳትም የእኛስ አምላክ ግሩም ነው በምክሩ
ፍፁም ነው አይሳሳትም የእኛስ አምላክ ግሩም ነው በምክሩ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ