አለ ጌታ
Ale Gieta
2007 · ትራክ 3 · 6:26 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሳስበው ልቤ ተነሳ
ውለታው እንዴት ይረሳ
ምክነያቱ እንዲህ መሆኔ
ስላለኝ ጌታ ከጎኔ (፪x)
አዝማች · Chorus
አለኝ ጌታ
አለኝ ኢየሱስ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ያ ሲሄድ መቶ ሳይቆይ
ሲሸሸኝ ከሩቅ አይቶኝ
ጌታ ግን ቤቴ ገብቶ
አሳየኝ ሁሉን ሰርቶ (፪x)
አሳየኝ ሁሉን ሰርቶ (፬x)
አለኝ ሚራራ
አለኝ የሚያዝን
አለኝ ሁል ጊዜ
አለኝ ልቡ ቅን
አለኝ አይከዳ
አለኝ አይተወኝ
አለኝ ያለሱ
አለኝ ማን አለኝ
አዝማች · Chorus
አለኝ ጌታ
አለኝ ኢየሱስ (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አይደለም እግረ መንገዴን
አምላኬን እኔስ መውደዴ
አለቴ ከሆነኝ ውዴ
ሰው ባለው አይኮራም እንዴ
አይደለም እግረ መንገዴን
አምላኬን እኔስ መውደዴ
አለቴ ከሆነኝ ውዴ
ባምላኬ አልኮራም እንዴ
አለኝ ሚራራ
አለኝ የሚያዝን
አለኝ ሁል ጊዜ
አለኝ ልቡ ቅን
አለኝ አይከዳ
አለኝ አይተወኝ
አለኝ ያለሱ
አለኝ ማን አለኝ
አዝማች · Chorus
አለኝ ጌታ
አለኝ ኢየሱስ (፬x)
ቁጥር 4 · Verse 4
አልፈራም ጌታ እንደሌለው
ጠላቴ ይጣ የሚለው
መንደሬን እሳቱ ከቧል
እኔ ያለኝ ከሰው ይለያል (፪x)
ያ ሲሄድ መቶ ሳይቆይ
ሲሸሽኝ ከሩቅ አይቶኝ
ጌታ ግን ቤቴ ገብቶ
አሳየኝ ሁሉን ሰርቶ (፪x)
አሳየኝ ሁሉን ሰርቶ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ