አያለሁ
Ayalehu
2007 · ትራክ 2 · 6:10 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የኑሮ መክበዱን ሁሉ ነገር መወደዱ
እህል ከጐተራ ሲጠፋ ፍሬም ባትሰጥ መሬት ታርሳ
ቀና ብሎ ዓይን ሲያይ ደመና የለም በላይ
ምድር ከሰማይ ይጠብቃል ሰማይ በምድር ላይ አፍጡዋል
ጊዜው ቢወስድ ይህ ዝምታ አምላኬ ምድሬን እየረሳ
ግን ጨለማው መበርታቱ ሊነጋ ነው ሌሊቱ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አያለሁ አያለሁ ገና ኦ ገና ብዙ አያለሁ
ቁጥር 3 · Verse 3
አያለሁ አያለሁ ገና ኦ ገና ብዙ አያለሁ
የእግዚአብሔር ክንድ በምድሬ ሲነሳ
የመከራው ዘመን ሲረሳ
እምባ ካለቀሰው ሲታበስ
የዘመናት/የአባቶቼ ጸሎት ሲመለስ (፪x)
አያለሁ አያለሁ ፣ አያለሁ አያለሁ
አዝማች · Chorus
አያለሁ አያለሁ ገና ገና ገና ብዙ አያለሁ
አያለሁ አያለሁ ገና ኦ ገና ብዙ አያለሁ
ቁጥር 4 · Verse 4
የጦርነት ድምጽ ፈርቶ
ካደገበት ቀይ ሸሽቶ
በሰው ሃገር አንገት የደፋ
የተናቀን የተገፋ
ምድረ በዳውን ሲያቋርጠው
በረሃው ሁሉም ሱያስጥለው
ግን ሃገሩን ይዞ በልቡ
ተበትኗል ሰሜን ደቡቡ
ተስፋ ቢጨልም በሁሉ ነገር
አንደበት ግን ክፉ አይናገር
ያለፈው ይብቃ እርግማኑ
የምትሰማ አያለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
አያለሁ አያለሁ ገና ገና ገና ብዙ አያለሁ
አያለሁ አያለሁ ገና ኦ ገና ብዙ አያለሁ
ቁጥር 5 · Verse 5
ሽባዎች አንካሶች ሲዘሉ
ዲዳዎች ተናግረው ዕልል ሲሉ
የታወረው ዓይን ሲበራ
እግዚአብሔር/የማመልከው እራሱ ሲሰራ
አያለሁ አያለሁ ፣ አያለሁ አያለሁ (፭x)
ሃሌሉያ አያለሁ
እኔ እኔ እኔ አያለሁ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ