እግዚአብሔር ትልቅ ነህ
Egziabhier Teleq Neh
2007 · ትራክ 8 · 7:20 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በዕውቀትህ ቀላያት ተቀደዱ
በማስተዋልህ ሰማያት ጸኑ
ጥበብህ ምድርን መሠረተ
ደመና ጠልን አንጠበጠበ
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ትልቅ ነህ
እግዚአብሔር ሃሌሉያ
እግዚአብሔር ትልቅ ነህ
እግዚአብሔር
ቁጥር 2 · Verse 2
አንተ ብቻ ነህ በመጀመሪያ ሰማይንና ምድርን የፈጠርከው
አንተ ብቻ ነህ ብርሃንን ደግሞ ከጨለማ የለየኸው
አንተ ብቻ ነህ ጠፈሩን ሰማይ የብሱንም ምድር ብለህ የጠራኸው
አንተ ብቻ ነህ የምድርን ባዶነት በቃልህ የሞላኸው
ይሁን ይሁን ብለህ ፈጥረህ በሙሉ የሆኑልህ
እንደተናገርከው የሆነ እንዳሰብከው የቆመልህ
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ትልቅ ነህ
እግዚአብሔር ሃሌሉያ
እግዚአብሔር ትልቅ ነህ
እግዚአብሔር
ቁጥር 3 · Verse 3
በዕውቀትህ ቀላያት ተቀደዱ
በማስተዋልህ ሰማያት ጸኑ
ጥበብህ ምድርን መሠረተ
ደመና ጠልን አንጠበጠበ
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ትልቅ ነህ
እግዚአብሔር ሃሌሉያ
እግዚአብሔር ትልቅ ነህ
እግዚአብሔር
ቁጥር 4 · Verse 4
አንተ ብቻ ነህ ተራሮችንም ኮረብቶችንም በሚዛን የመዘንከው
አንተ ብቻ ነህ የምድርን አፈር በመስፈሪያ የሰበሰብከው
አንተ ብቻ ነህ ከጥንት ጀምሮ በምድር ክበብ ላይ የተቀመጥከው
አንተ ብቻ ነህ አማካሪ አትፈልግ ጥበብህ ቁጥር የሊለው
ይሁን ይሁን ብለህ ፈጥረህ በሙሉ የሆኑልህ
እንደተናገርከው የሆነ እንዳሰብከው የቆመልህ
ንግስናና ክብርን የለበስህ
በማስተዋል እጅቅ ድንቅ የሆንህ
ሃሳብህ ጥልቅ የማይመረመር
ካልኩት በላይ ትልቅ ነህ እግዚአብሔር
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ትልቅ ነህ
እግዚአብሔር ሃሌሉያ
እግዚአብሔር ትልቅ ነህ
እግዚአብሔር
ቁጥር 5 · Verse 5
አንተ ብቻ ነህ ፍጥረት በሙሉ በፊትህ ወድቆ የሚሰግድልህ
አንተ ብቻ ነህ ሁሉን የምትገዛ እኩያ አምሳያ የለህ
አንተ ብቻ ነህ ምንም ነገር ሳይኖር ከሁሉ በፊት ብቻህን የነበርከው
አንተ ብቻ ነህ ሁሉመ ነገር ሲያልፍ ሲጠቀለል የምትኖረው
ታዲያ ይህን ሁሉ ያየ አትኩሮ ያስተዋለ
ትልቅ ነህ ከማለት በቀር የሚለው ሌላ ምን አለ
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ትልቅ ነህ
እግዚአብሔር ሃሌሉያ
እግዚአብሔር ትልቅ ነህ
እግዚአብሔር
ቁጥር 6 · Verse 6
ንግስናና ክብርን የለበስህ
በማስተዋል እጅቅ ድንቅ የሆንህ
ሃሳብህ ጥልቅ የማይመረመር
ካልኩት በላይ ትልቅ ነህ እግዚአብሔር
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ትልቅ ነህ
እግዚአብሔር ሃሌሉያ
እግዚአብሔር ትልቅ ነህ
እግዚአብሔር
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ