እንዳንተ የለም
Endante Yelem
2007 · ትራክ 10 · 6:02 · አማርኛ
የአማልክት አምላክ ነህ የነገስታት ንጉስ
የሚመስልህ የሌለህ የእግዚአብሔር ልጅ እየሱስ
አመልክሃለሁ/4X/
መጥቻለሁ በፊትህ ላመልክህ ነው
አስቀድሜ በእግርህ ስር እሰግዳለው
ቀና ብዬ አንተን ሳይ ተውበሃል
የምስጋናን የክብርን ዘውድ ጭነሃል
እጨምራለው በሞገስ ላይ ሞገስ ንጉሴ ሆይ
ከዚህም በላይ ንገስ ባማረ ዜማ
በተዋበ እልልታ ይድመቅ ዙፋንህ
ተመለክ ተውደስ የኔ ጌታ
እኔም አላውቅህም አምላኬ ትልቅ ነህ
ከአይምሮዬም በላይ ሆነ ማንነትህ /2X/
ከፍ ባለ ዙፋን ላይ የተቀመጥቀው
ብርሃንን እንደ ልብስ የለበስከው
ማዕረግህ ስልጣንህ የብቻህ ነው
በሹመትስ የተሾመ እንዳንተ ማነው
እጨምራለው በሞገስ ላይ ሞገስ ንጉሴ ሆይ
ከዚህም በላይ ንገስ ባማረ ዜማ
በተዋበ እልልታ ይድመቅ ዙፋንህ
ተመለክ ተውደስ የኔ ጌታ
እኔም አላውቅህም አምላኬ ትልቅ ነህ
ከአይምሮዬም በላይ ሆነ ማንነትህ /2X/
በክብር ማነው እንዳንተ ክቡር ማነው
ኧረ ማነው እንዳንተ ያለ ማነው
በሞገስ ማነው እንዳንተ ሞገሳም ማነው
ኧረ ማነው እንዳንተ ያለ ማነው
በሀይል ማነው እንዳንተ ሀያል ማነው
ኧረ ማነው እንዳንተ ያለ ማነው
በስልጣን ማነው እንዳንተ ባለስልጣን ማነው
ኧረ ማነው እንዳንተ ያለ ማነው
በአማልክት ማነው እንዳንተ አምላክ ማነው
ኧረ ማነው እንዳንተ ያለ ማነው
በፍጹም የለም እንዳንተ ያለ የለም/2X/
አይኖርም የለም እንዳንተ ያለ የለም/2X/
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ