አምንሃለው
Amnihalehu
ትራክ 10 · 5:14 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሁሉን የምትችል የአብርሃም አምላክ
ስለ ተስፋ ቃልህ ቅዱስ ስምህ ይባረክ
በእምነት በመጽናት ክብርህን ሰጥሃለው
አልጠራጠርም ቃልህን አምናለው
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ሆይ እኔ አምንሃለው
ከማየው በላይ ቃልህን አምናለው
በምንም አይነት እንደማተወኝ
የከፈልክብኝ እየሱስ አሳየኝ
እግዚአብሔር ሆይ እኔ አምንሃለው
ቁጥር 2 · Verse 2
ከራሴ በላይ ቃልህን አምናለው
በዙፋንህ ላይ እንደምትኖር ፀንትህ
ለሚወዱህም ዋጋን እየሰጠህ
ከጠየኩህ እና ከማስበው በላይ
ማድረግ ለሚቻልህ ያለ አንዳች ከልካይ
ተስፋን በሚያስቆርጥ ባለቀ ነገር ላይ
ህይወት የምትዘራ አንተ አደለህም ወይ
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ሆይ እኔ አምንሃለው
ከማየው በላይ ቃልህን አምናለው
በምንም አይነት እንደማተወኝ
የከፈልክብኝ እየሱስ አሳየኝ
እግዚአብሔር ሆይ እኔ አምንሃለው
ቁጥር 3 · Verse 3
ከራሴ በላይ ቃልህን ይዣለው
በዙፋንህ ላይ እንደምትኖር ፀንትህ
ለሚወዱህም ዋጋን እየሰጠህ
በእምነት ጠብቃለው ቃልህን በተስፋ
የሚታይ ደመና ለጊዜው ቢጠፋ
ሃይሌ አንተ ነህና ፍጹም አልታክትም
በአንተ የታመኑትን ከቶ አትጥላችሀውም
ክንድህን ታምኜ ባንተ እመካለው
የነገርከኝን ተስፋ አደርጋለው
በቃልህ ታማኝ አምላክ ነህና
እጠብቅሃለው ሆኜ በምስጋና (፫X)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ