ይመጣል
Yimetal
ትራክ 13 · 5:19 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እንዴት እንሆን ይሆን ፊትለፊት ስናየው
ያዘጋጀነውን ጥያቄ ትተነው
ፈዘን በውበቱ በሚያስደንቅ ግርማው
አይን አይኑን እያየን እሱን ማወደስ ነው
ይመጣል በግርማው ይመጣል በክብር
ሊወስደን እንድንኖር ከእርሱ ጋር
ተስፋችን ኢየሱስ በሀይል ይገለጣል
የወጉትም ደግሞ በአይናቸው ያዩታል
አዝማች · Chorus
የእርሱ የሆኑትን ግን ሊወስድ ይመጣል
ማደሪያው ከእኛ ጋር ነው እግዚአብሔር እራሱ
ህመም ወይም ሀዘን በዛ አይሠማም
እንባችንን በሙሉ ታብሶ ከአይናችን
ከኢየሱስ ጋር ልንኖር አብረን እንሄዳለን
አዝማች · Chorus
ይመጣል በግርማው ይመጣል በክብር
ሊወስደን እንድንኖር ከእርሱ ጋር
ተስፋችን ኢየሱስ በሀይል ይገለጣል
የወጉትም ደግሞ በአይናቸው ያዩታል
የእርሱ የሆኑትን ግን ሊወስድ ይመጣል
ቁጥር 2 · Verse 2
አዲሷ ኢየሩሳሌም ውበቷ የከተማው
የእግዚአብሔር ክብር እና በጉ ብርሀኗ ነው
ፀሀይ ወይም ጨረቃ ከቶ አያስፈልግም
የአምላኬ መገኘት ያበራዋል ሁሉንም
እንሄዳለን በክብር ልንኖር ከእርሱ ጋር
ይመጣል በክብር ልንኖር ከእርሱ ጋር
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ