አፀደቀን
Atsedeken
ትራክ 1 · 5:46 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ክብር ምስጋና ይሁን ለእግዚአብሄር
ወዶናልና ከቶ ላይተወን በዘላለም ፍቅር
ክብር ምስጋና ይሁን ለእግዚአብሄር
በእራሱ ምሏል ከቶ ላይተወን ታላቅ እርስት ሆነን
ወድቀን ሳለን ተጥለን ስንጨነቅ ሚረዳን አተን
በደም ተለዉሰን ሳለን በብዙ ስቃይ ተስፋ ቆርጠን
አይቶ እጅግ እራራልን ቁስላችንን አጥቦ ፈወሰን
ልጁን በወደደበት ፍቅር እኛንም እንዲሁ ወደደን
አዝማች · Chorus
አዳነን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑም ጠራን
የእርሱን ፍቅር በጎነት እንድንናገር ተመረጥን
ታላቅ ህዝብ አደረገን የተለየን የንጉስ ካህን
ምህረትን አግኝተን ተባልን የእግዚአብሄር ወገን
ወገን /3/ ወገን : አደረገን
ልጆች /3/ ልጆቹ : አረገን
አፀደቀን...
ቁጥር 2 · Verse 2
አምላክ ተብሎ ሊጠራብን እግዚአብሄር ስላላፈረብን
ከእርሱ ጋር አብረን እንድንኖር በሰማይ ስፍራ አዘጋጀልን
ወደደን ደግሞም አፀደቀን ከእንግዲ ማነው ሚኮንነን
ሰቶናል የልጅነት መንፈስ እንድንጠራው አብ አባት ብለን
አዝማች · Chorus
አዳነን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑም ጠራን
የእርሱን ፍቅር በጎነት እንድንናገር ተመረጥን
ታላቅ ህዝብ አደረገን የተለየን የንጉስ ካህን
ምህረትን አግኝተን ተባልን የእግዚአብሄር ወገን
ወገን /3/ ወገን : አደረገን
ልጆች /3/ ልጆቹ : አረገን
አፀደቀን...
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ