አስደስተዋለሁ
Asdesetewalehu
2002 · ትራክ 6 · 10:10 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ቤትህ በምን ላይ ነው የተመሠረተው
ቤትህ በምን ላይ ነው የተመሠረተው
በአለት ነው በአሸዋ ቤትህ በምን ላይ ነው (፪x)
ቤቴ አሸዋ ላይ ነው የተመሠረተው
እስከአሁን ሰላም ነው ችግርም አላየሁ
በጋው ተስማምቶኛል ምን ችግር ይመጣል
ውኃ እኮ በአሸዋ ወዲያው ይመጠጣል
"መስሎሃል"
ይልቅ ወጪ አታውጡ አለት አትቧጥጡ
ወጪን ይቀንሳል አሸዋ እኮ ሞልቷል
የእኔስ ቤት አምራለች በጣም ዘንጣለች
ላለሁበት ጊዜ ተመችታኛለች
"ተው ይቅርብህ"
አዝማች · Chorus
አሸዋ ከሆነ የቤትህ መሠረት (፪x) አቤት ጉድ ፈላበት
አሸዋ ከሆነ የቤትህ መሠረት (፪x) አቤት ጉድ ፈላበት
ቁጥር 2 · Verse 2
ክረምት የመጣ ቀን ፤ ዝናብ የመጣ ቀን
ጐርፉ የመጣ ቀን ፤ ንፋስ የመጣ ቀን
ጠራርጐ ይወስደዋል አንዱንም ሳያስቀር
ገንዘብህ ከሆነ የሕይወትህ መሠረት
ዕውቀትህ ከሆነ የሕይወትህ መሠረት
አቤት ጉድ ፈላበት
ሥልጣንህ ከሆነ የሕይወትህ መሠረት
ጥበብህ ከሆነ የሕይወትህ መሠረት
አቤት ጉድ ፈላበት
ችግር የመጣ ቀን ፤ ሃዘን የመጣ ቀን
መከራ የመጣ ቀን ፤ ማጣት የመጣ ቀን
ጠራርጐ ይወስደዋል አንዱንም ሳያስቀር
ቁጥር 3 · Verse 3
ቤትህ በምን ላይ ነው የተመሠረተው
ቤትህ በምን ላይ ነው የተመሠረተው
ባለት ነው በአሸዋ ቤትህ በምን ላይ ነው (፪x)
ቤቴ በዓለት ላይ ነው የተመሠረተው
ችግሩም በሽበሽ ነው መከራብ ብዙ ነው
ጐርፉ ሲወርድብኝ ነፋስ ሲነፍስብኝ
አለት ላይ ስላለሁ ቤቴ አልፈረሰብኝ
"ኧረ ምንም አትሆን"
አለት በቀላሉ አይገኝም ሲሉ
የምደክም መስሎኝ ድሮ ተሞኘሁኝ
የአሸዋ ነጋዴው ነበርና ወሬው
ቤቴን በዓለት ብቻ ሰራሁ ከነአካቴው
"ደግ አድርገሃል"
አዝማች · Chorus
አለቱ ከሆነ የቤትህ መሠረት
አለቱ ከሆነ የቤትህ መሠረት
በቃ አለፈለት (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ክረምቱ ቢመጣ ፤ ዝናቡም ቢወርድ
ጐርፉ ቢንደረደር ፤ ንፋሱም ቢነፍስ
የአንተ ቤት እንደሆን ፈጽሞ አይላወስ
ኢየሱስ ከሆነ የሕይወትህ መሠረት
ቃሉ ከሆነልህ የሕይወትህ መሠረት
በቃ አለፈለት (፪x)
መከራ ቢመጣ ፤ ችግር ቢደርስብህ
ሃዘን ቢያጋጥምህ ፤ ማጣት ቢያስቸግርህ
አትነቃነቅም አለት ላይ ስላለህ
አዝማች · Chorus
አለቱ ነው መሠረቴ (፬x)
ኢየሱስ ነው መሠረቴ (፬x)
አለቱ ነው መሠረቴ (፬x)
ኢየሱስ ነው መሠረቴ (፬x)
ያየሁት በስጋ ዓይን አይደለም ግን እርግጠኛ ነኝ
በሕይወቴ አይቼዋለሁ ፍቅሩ ሲዳስሰኝ (፬x)
አለቱ ነው መሠረቴ (፬x)
ኢየሱስ ነው መሠረቴ (፬x)
አለቱ ነው መሠረቴ (፬x)
ኢየሱስ ነው መሠረቴ (፬x)
ያየሁት በስጋ ዓይን አይደለም ግን እርግጠኛ ነኝ
በሕይወቴ አይቼዋለሁ ፍቅሩ ሲዳስሰኝ (፬x)
አለቱ ነው መሠረቴ (፬x)
ኢየሱስ ነው መሠረቴ (፬x)
አለቱ ነው መሠረቴ (፬x)
ኢየሱስ ነው መሠረቴ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ