እግዚአብሔርን መምሰል
Egziabhieren Memsel
2002 · ትራክ 7 · 5:00 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ለሥጋዊ ነገር እራስን ማስለመድ
ከእግዚአብሔር ሀሳብ እርቆ መራመድ
ለጊዜያዊ ደስታ ነፍስን አስገዝቶ
ዛሬን ብቻ መኖር የነገውን ትቶ
አይጠቅመኝም ከቶ ይህን አውቄዋለሁ
እግዚአብሔርን መምሰል ለእኔ ማትረፊያ ነው
ብዬ ተናግሬ ጉዞ ጀምሬያለሁ
ጥማቴም ናፍቆቴም ጌታዬን መምሰል ነው
አዝማች · Chorus
በሰው ወግ ተይዞ በይሉኝታ እስራት
ዛሬን ላያሻግር ለእንጀራ መገዛት
እውነትን ከመግለጥ በውሸት ከልሎ
መምሰል የሌለበት የማስመሰል ኑሮ
አይጠቅመኝም ከቶ ይህን አውቄዋለሁ
እግዚአብሔርን መምሰል ለእኔ ማትረፊያ ነው
ብዬ ተናግሬ ጉዞ ጀምሬያለሁ
ጥማቴም ናፍቆቴም ጌታዬን መምሰል ነው
ቁጥር 2 · Verse 2
ታላቅና ክቡር ሕይወትም የሆነ
ከአማራጮች ሁሉ እጅግ የተሻለ
አሁን ላለውና ለመጪው ዘመኔ
እግዚአብሔርን መምሰል ያዋጣኛል ለእኔ
ያዋጣኛል አዎ ይህን አውቄያለሁ
እግዚአብሔርን መምሰል ለእኔ ማትረፊያ ነው
ብዬ ተናግሬ ጉዞ ጀምሪያለሁ
ጥማቴም ናፍቆቴም ጌታዬን መምሰል ነው
ቁጥር 3 · Verse 3
ከኋላ ያለውን በሙሉ ረስቼ
የፊቴን ለመያዝ እጆቼን ዘርግቼ
ምልክት አይቼ መፍጠን ጀምሬያለሁ
መጠራቴ ዋጋው ጌታዬን መምሰል ነው
ብዬ ተናግሬ ጉዞ ጀምሬያለሁ
እግዚአብሔርን መምሰል ለእኔ ማትረፊያ ነው
ስለዚህ የሚይዘኝ የሚያስቀረኝ ማነው
ሁሉንም እየጣስኩ ወደፊት ሄዳለሁ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ