ሥራህን ትፈፅማለህ
Serahen Tefetsemaleh
2002 · ትራክ 3 · 5:13 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በዘመን በዓመታት መሃል
ሥራህን ትፈፅማለህ
የሚከለክልህ ማነው
ኢየሱስ ኃይልህ ብርቱ ነው (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ባለፈው ዘመን የሰራ ዛሬም ክንዱ ያልደከመ
መንግሥቱን በደንብ አስፋፋ እኛም ደግሞ የቀጠለ
ኃይል ብርታት ጉልበት ሆኖልን የምንሰራው አብረን ነው
አሁን ካሳየን ይበልጣል ነገን በእኛ የሚገልጠው
ሰራተኛ አድርጐናል ለቤቱ
መስራት ያላቆመ ከጥንቱ
በሚሰራበት ቀን በቤቱ
መጠቀሚያው ነን እኛ ገንዘቡ (፪x)
አዝማች · Chorus
በዘመን በዓመታት መሃል
ሥራህን ትፈፅማለህ
የሚከለክልህ ማነው
ኢየሱስ ኃይልህ ብርቱ ነው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በአሁኑ ዓመት እንዳየነው በሚመጣው ዓመት አይሆንም
ብሶበት እንጂ ቀንሶ ሥራው አይከናወንም
እጥፍ ድርብ እየሆነ ፍሬው ገና ይበዛልናል
በክልል አይወሰንም የምድርን ፊት ይሸፍናል
የምሩን ይነሳል ንጉሡ
እናንተ አገልጋዮች ተነሱ
ገና ብዙ ጉድ ነው የሚታየው
እግዚአብሔር ሀሳቡ እኛ ላይ ነው (፪x)
አዝማች · Chorus
በዘመን በዓመታት መሃል
ሥራህን ትፈፅማለህ
የሚከለክልህ ማነው
ኢየሱስ ኃይልህ ብርቱ ነው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ዛሬ ከተገለጠልን የነገው ደግሞ ይብሳል
የሚመጣልን ዝማሬ የዛሬን ሁሉ ያስረሳል
ማሽቆልቆል ወደታች መውረድ መቀነስ መዳከም መዛል
ከዚህ በኋላ በእኛ ላይ በኢየሱስ ሥም አይሰራም
ተሻገር የሚል ወደ ማዶ
ሰምተናል ድምፅ ከሰማይ ወርዶ
ተሻግረን ደግሞ እንሄዳለን
የነገውን ዘመን እናያለን (፪x)
አዝማች · Chorus
በዘመን በዓመታት መሃል
ሥራህን ትፈፅማለህ
የሚከለክልህ ማነው
ኢየሱስ ኃይልህ ብርቱ ነው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ