አይቼዋለሁ
Ayechewalehu
ትራክ 3 · 4:38 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ምህረትህ ጌታዬ ምህረትህ
ምህረትህ አምላኬ ምህረትህ
ከአንተ የተነሳ ነው
ለዚህ መድረሴ (፬x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ምህረትህ እንዴት በዝቷል
ከፍ ብሏል ለእኔስ ገኗል (፪x)
በበደሉ ምክንያት ጠፍቶ የነበረው ሰው
ከጥፋት ጐዳና በፍቅርህ መለስከው
የክህነቱን ስራ ኑሮው አድርጐታል
ያዳነውን አምላኩን ሁሌ ይቀድሰዋል (፪x)
አዝማች · Chorus
ምህረትህ (፬x) ለእኔ በዝቷል
ምህረትህ (፬x) ለእኔ በዝቷል
በብዙዎችም መካከል (አመሰግንሃለሁ)
ቸርነትህ ምድርን ሞልቷል (እዘምረዋለሁ)
የስምህ ትርጉም ገብቶኛል (ሁሌ እጠራዋለሁ)
ብብዙዎችም መካከል (አመሰግንሃለሁ)
ቸርነትህ ምድርን ሞልቷል (እዘምረዋለሁ)
ኢየሱስ ማለት ገብቶኛል (ሁሌ እጠራዋለሁ)
ቁጥር 2 · Verse 2
ንጉሥ ንጉሥን ሲሽረው
ኃያል ኃያሉን ሲያወርደው
ጊዜው/አንዱ ሲያልፍ ሲተካ በሌላ ጌታ
ኢየሱስ ግን ሁሌ የጌቶች ጌታ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አይቼዋለሁ ኦሆሆ እኔም በኑሮዬ አሃሃ
አመታት አለፉ አላለፈም ጌታዬ
አይቼዋለሁ ኦሆሆ እኔም በኑሮዬ አሃሃ
ዘመናት አለፉ አላለፈም ጌታዬ
አይቼዋለሁ ኦሆሆ እኔም በኑሮዬ አሃሃ
ኃያላን አለፉ አላለፈም ጌታዬ
አይቼዋለሁ ኦሆሆ እኔም በኑሮዬ አሃሃ
ብዙዎች አለፉ አላለፈም ጌታዬ
ቁጥር 4 · Verse 4
ሲመሽ ሲነጋ ጠዋት ማታ
አመልከዋለሁ ይህን ጌታ (፪x)
ሲመሽ ሲነጋ ጠዋት ማታ
ሾመዋለሁ በከፍታ (፪x)
ሲመሽ ሲነጋ ሁሌ ማታ
አስበዋለሁ በመኝታ (፪x)
ሲመሽ ሲነጋ ጠዋት ማታ
እደነቃለሁ በዚህ ጌታ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ