ከፍ በል
Kef Bel
ትራክ 2 · 5:26 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በዚያ በክፉ ቀን በጨለማ (፪x)
እግዚአብሔር ብቻ ጩኸቴን ሰማ (፪x)
ደጃፌን ዘግቼ ያኔ የነገርኩህ (፪x)
ያን ቀን ታስቦልኝ በእርሱ በዓይኔ አየሁህ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አቤት ጌታዬ ምስኪኑን ሲረዳ
አቤት ኢየሱሴ ሲደርስ ለተጐዳ
አየሁ ጌታዬ ምስኪኑን ሲረዳ
አየሁ ኢየሱሴ ሲደርስ ለተጐዳ
እርሱንማ በእውነት ለሚጠሩ
የቅርብ እንጂ አይደለም የሩቅ
ጌታንማ በእምነት ለሚጠሩ
የቅርብ እንጂ አይደለም የሩቅ (፪x)
አዝማች · Chorus
ከፍ በል ከሁሉ በላይ (፪x)
እርካታዬ ስትከብር ሳይ (፪x)
ከፍ በል ከሁሉ በላይ (፪x)
ተድላዬ ስትከብር ሳይ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በጉባኤ መሃል ስትከብር እያየሁ
እንዴት ችዬ ዝም እላለሁ እንዴት ችላለሁ
ሕዝብህ ሲያደንቅህ እያየሁ
እንዴት ችዬ ዝም እላለሁ እንዴት ችላለሁ
አምሮብህ ተውበህ እያየሁ
እንዴት ችዬ ዝም እላለሁ እንዴት ችላለሁ
ከፍ በል ከሁሉ በላይ (፪x)
ሹመቴ ስትከብር ሳይ (፪x)
ከፍ በል ከሁሉ በላይ (፪x)
ድምቀቴ ስትከብር ሳይ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ችግረኛ ሲጮህ ሰምተህ ዝም አትልም (፪x)
የምስኪኑን ውድቀት አይተህ እንዳላየህ አትሆንም (፪x)
እጅህን ዘርግተህ ሁሉን ትረዳለህ (፪x)
አደራረግህ ግሩም ነው ከሰው ልዩ ነህ (፪x)
አቤት ጌታዬ ምስኪኑን ሲረዳ
አቤት ኢየሱሴ ሲደርስ ለተጐዳ
አየሁ ጌታዬን ምስኪኑን ሲረዳ
አየሁ ኢየሱሴ ሲደርስ ለተጐዳ
እርሱንማ በእውነት ለሚጠሩ
የቅርብ እንጂ አይደለም የሩቅ
ጌታንማ በእምነት ለሚጠሩ
የቅርብ እንጂ አይደለም የሩቅ (፪x)
አዝማች · Chorus
ከፍ በል ከሁሉ በላይ (፪x)
እርካታዬ ስትከብር ሳይ (፪x)
ከፍ በል ከሁሉ በላይ (፪x)
ተድላዬ ስትከብር ሳይ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
መቃብር ተከፍቶ እያየሁ
እንዴት ችዬ ዝም እላለሁ እንዴት ችላለሁ
ድንጋይ ተንከባሎ እያየሁ
እንዴት ችዬ ዝም እላለሁ እንዴት ችላለሁ
ዲያቢሎስ ሲረገጥ እያየሁ
እንዴት ችዬ ዝም እላለሁ እንዴት ችላለሁ
ከፍ በል ከሁሉ በላይ (፪x)
ሹመቴ ስትከብር ሳይ (፪x)
ከፍ በል ከሁሉ በላይ (፪x)
ድንቀቴ ስትከብር ሳይ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ