ልዑል እግዚአብሔርን
Leul Egziabhieren
ትራክ 5 · 5:47 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አቤኔዘር አቤኔዘር እግዚአብሔር ረዳን
አቤኔዘር አቤኔዘር እግዚአብሔር ረዳን
ቁጥር 1 · Verse 1
እስካሁን እግዚአብሔር ረዳን
እስካሁን እግዚአብሔር እረዳን (፪x)
እኛም ደግሞ የረዳንን
ልዑል እግዚአብሔርን እናመልካለን
. (1) . ኮረብቶች ወንዞችን አፈሰሱ
በሸለቆችም መካከል ምንጮች ተከፈቱ
ምድረበዳው ረሰረሰ ከጥማት ምድር ውኃ ፈለቀ
እግዚአብሔር አምላክ የእኛን ጩኸት አደመጠ
በእኛ ላይ ታወቀ
አዝማች · Chorus
አቤኔዘር አቤኔዘር እግዚአብሔር ረዳን
አቤኔዘር አቤኔዘር እግዚአብሔር ረዳን
ቁጥር 2 · Verse 2
ብቻውን እግዚአብሔር ረዳን
ብቻውን እግዚአብሔር እረዳን (፪x)
እኛም ደግሞ የረዳንን
ልዑል እግዚአብሔርን እናመልካለን
ወጥመድ ቢዘረጋ አሃሃሃሃ ጉድጓድም ቢቆፍር
ጠላቴ ሊይዘኝ ሊያጠፋኝ ቢሞክር
ቢመስለኝም ምወድቅ ፈጽሞ ምጠፋ
ጌታዬ ሆኖኛል የዘለዓለም ተስፋ አሜን
ስለዚህ አለሁ አልጠፋሁም
ሸንበቆን አልተደገፍኩም
ይረዳኛል ኃይሌ ነው
በአምላኬ ቅጥሩን እዘላለሁ (፪x)
አምላክ ነህና አምላክ ነህና (፪x)
ላምልክህ እንደገና (፬x)
አምላክ ነህና ላምልክህ እንደገና
አምላክ ነህና ላምልክህ እንደገና
አንዳንዶች የሰይጣን ቀንበሩ ከብዷቸው
ጅማሬ ላይ ቀሩ ጠፍቶ ሚረዳቸው
ሲያገለግሉ ሰይጣንን ደፋ ቀና ሲሉ
ተሰብሮ ወጋቸው ምርኩዙ ጠፍተው በዚያው ቀሩ
እኔ ግን አለሁ አልጠፋሁም
ቀንበር ከብዶኝ አልጐበጥኩም
ቀና ብዬ እሄዳለሁ
በአምላኬ ቅጥሩን እዘላለሁ
በፀጋሁ አለሁ አልጠፋሁም
ቀንበር ከብዶኝ አልጐበጥኩም
ቀና ብዬ እሄዳለሁ
በአምላኬ ቅጥሩን እዘላለሁ
ከአንተ በቀር ሌላ ሌላ አምላክ ማነው?
ሌላ አምላክ ማነው? (፪x)
ሳስብህ ደስ ይለኛል
ኩራትም ይሰማኛል
ከልቤ ደስታ ፈንቅሎ
አዘለለኝ ወጣሁ ከእሮሮ (፭x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ