Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እንዳንተ ያለ የለም

Endante Yale Yelem

ትራክ 4 · 5:52 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ስለሰራኸው ስራ ስላደረከው ነገር

ስለሰራኸው መዳን ስላደረከው ተዓምር

ምን እንከፍልሃለን ተመስገን (፬x)

እንዳንተ ያለ የለም (፪x)

እንዳንተ ያለ የለም እላለሁ (፪x)

እንዳንተ ያለ የለም (፪x)

እንዳንተ ያለ የለም እላለሁ (፪x)

ብርሃንህን በልቤ አብርተህልኛል

ጨለማዬን ሁሉ ገፈህልኛል

አቤቱ ከልቤ ላመስግንህ(፪x)

ኢየሱስ ከልቤ ላመስግንህ(፪x)

በእኔ ላይ እንዳይሰለጥን የቀድሞው ጨለማ

የዋይቶ የለቅሶ ድምጽ ከእንግዲህ እንዳይሰማ (፪x)

ሕይወቴን ለውጧል ብርሃንህ በውስጤ

ብሩህ ተስፋ አያለሁ ለቀረው ዘመኔ

አቅጣጫን ለውጧል አላማህ በውስጤ

ብሩህ ተስፋ አያለሁ ለቀረው ዘመኔ

ብርሃንህን በልቤ አብርተህልኛል

ጨለማዬን ሁሉ ገፈህልኛል

አቤቱ ከልቤ ላመስግንህ(፪x)

ኢየሱስ ከልቤ ላመስግንህ(፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ