Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

በአንተ ደስ ይለኛል

Bante Des Yilegnal

2005 · ትራክ 5 · 6:04 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አምልኮና ስግደት የተገባህ (የተገባህ) የተገባህ ነህ

አልፋና ኦሜጋ መጀመሪያ (መጀመሪያ) መጨረሻ የለህ (፪x)

(መንፈስ ቅዱስ) ክቡር ነህ ቅዱስ ነህ ጌታ

(መንፈስ ቅዱስ) አመልክሃለሁኝ ጠዋት ማታ

(መንፈስ ቅዱስ) አምላኬ ነህ አንተ ፈጣሪ

(መንፈስ ቅዱስ) እስትንፋሴ የነፍሴ ሰሪ

አዕላፋት ቅዱስ የሚሉህ

ሌት ተቀን የሚዘምሩልህ

አንተ ነህ አምላኬ/ንጉሤ ገናና

ላምልክህ/ላክብርህ ይገባሃልና (፪x)

አምልኮና ስግደት የተገባህ (የተገባህ) የተገባህ ነህ

አልፋና ኦሜጋ መጀመሪያ (መጀመሪያ) መጨረሻ የለህ (፪x)

(መንፈስ ቅዱስ) ክቡር ነህ ቅዱስ ነህ ጌታ

(መንፈስ ቅዱስ) አመልክሃለሁኝ ጠዋት ማታ

(መንፈስ ቅዱስ) አምላኬ ነህ አንተ ፈጣሪ

(መንፈስ ቅዱስ) እስትንፋሴ የነፍሴ ሰሪ

ዙፋንህ ከጥንት ጅምር

ጽኑ ነው ማን ሊደፍረው ቀድሞ

ግዛትህ የለው መጨረሻ

ታላቅ ነህ አንተ የእኔ ጋሻ

የሰላሜ ምንጭ ነህ የእረፍቴ ጌታ

በአንተ ደስ ይለኛል አግኝቻለሁ እርካታ

አመልክሃለሁ ሁልጊኤ ከነፍሴ አንተ ነህ ንጉሤ

ንጉሤ አንተ ነህ ንጉሤ

ወድሃለሁ እውድሃለሁ ወድሃለሁ እወድሃለሁ

አምላኬ ነህ ንጉሤ ነህ አንተን ሾሜሃለሁ

የግሌ ነህ የራሴ ነህ አንተን መርጫለሁ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ