በማለዳ ምሥጋና
Bemaleda Mesgana
2005 · ትራክ 8 · 6:42 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የሚረዳኝ የለም ከአንተ ሌላ
የውስጥ ብሶቴን ጭንቄን ሚያሟላ
እድል ፈንታዬ አንተው ነህና
አዋይሃለሁ አጫውትሃለሁ
ማን አለኝ ከአንተ ሌላ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ዞሬያለሁኝ በዓለም ተስፋ አገኝ መስሎኝ
በከንቱ ዘመኔን እንዲያው ጨረስኩኝ
የምታዛልቀኝ አንተው ብቻ ነህ
ተረድቻለሁ ና
እምባዬን አብስ ተስፋዬን አድስ
ከማህጸን ጀምሮ ተሸክመኸኛል
እንደ ልጅ አባብለህ አሳድገኸኛል
ከአንተ ወዲያ ለእኔ የለኝም የማውቀው
ኧረ ፊትህ ወድቄ እማጸንሃለሁ
ጌታ ጌታ የእኔ ማረፊያ
ጌታ አለሁልህ በለኝና
እስኪ ልረፍ ድምጽህን ልስማ
ከአንተ ወዴት እሄዳለሁ
መጠጊያዬን አውቃለሁ
አዝማች · Chorus
የሚረዳኝ የለም ከአንተ ሌላ
የውስጥ ብሶቴን ጭንቄን ሚያሟላ
እድል ፈንታዬ አንተው ነህና
አዋይሃለሁ አጫውትሃለሁ
ማን አለኝ ከአንተ ሌላ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ወደ ቀኝ ወደ ግራ ተመለከትኩኝ
ተስፋ የሚሆነኝ አንድም አጣሁኝ
መሸሸጊያዬ ለእኔ መድሃኒት
ለነፍሴ ጌታ ና
ከእስራት ፍታኝ ልጄ ነህ በለኝ
ብዙ ነገር አለኝ እኔስ የማጫውትህ
የልቤን የውስጤን ሁሉንም ልንገርህ ኢየሱስ
ነፍሴ በእጅህ ናት መላው አካላቴ
ፈቃድህ ይሁንልኝ ያልከው በሕይወቴ
ጌታ ጌታ የእኔ ማረፊያ
ጌታ አለሁልህ በለኝና
እስኪ ልረፍ ድምጽህን ልስማ
ከአንተ ወዴት እሄዳለሁ
መጠጊያዬን አውቃለሁ
አዝማች · Chorus
የሚረዳኝ የለም ከአንተ ሌላ
የውስጥ ብሶቴን ጭንቄን ሚያሟላ
እድል ፈንታዬ አንተው ነህና
አዋይሃለሁ አጫውትሃለሁ
ማን አለኝ ከአንተ ሌላ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ