Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ቤተክርስቲያን

Bietekrestiyan

2005 · ትራክ 10 · 5:41 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ቤተክርስቲያን ሙሽራይቱ

ሙሽራሽ ሊመጣ ጊዜው አይደለም ወይ

አጊጠሽ ጠብቂ ተዘጋጂ ቶሎ

ሙሽራሽ ይመጣል መላዕክት አስከትሎ

በመላዕክት ታጅቦ ኦሆ

የቀድሞ ፍቅርሽን አድሺ በጊዜ

ከአንቺ ይወገዱ ድካም ድንዛዜ

ንቂ መብራት አብሪ ተዘጋጂ ፈጥነሽ

ጠብቂው ኢየሱስን ጌጠኛ ልብስ ለብሰሽ

ያማረ ልብስ ለብሰሽ አዎ

በራድ ወይም ትኩስ ከቶም አይደለሽ

እስካሁን ኖረሻል እንዲያው ለብ ብለሽ

ትምክህትሽን ጣዪ አትበይ ሁሉ አለኝ

ኋላ እንዳታጪ ሊመጣ ያለውን

ሊገለጥ ያለውን አዎ

ቤተክርስቲያን ሙሽራይቱ

ሙሽራሽ ሊመጣ ጊዜው አይደለም ወይ

አጊጠሽ ጠብቂ ተዘጋጂ ቶሎ

ሙሽራሽ ይመጣል መላዕክት አስከትሎ

በመላዕክት ታጅቦ ኦሆ

በፈሰሰልሽ ደም ጉድፍሽኝ አጥሪ

ቀን ሳለ በጊዜ ራስሽን መርምሪ

ኩል ግዢ ከጌታ ዓይንሽ ይከፈታል

የጐደለሽ ሁሉ ያኔ ይታይሻል

ያኔ ይታይሻል አዎ

ኩራዝሽን አብሪ ዘይቱንም ግዢ

ምንም እንዳይጐድልሽ ትጊ ተጠንቀቂ

የምትጠብቂው ሙሽራ ይመጣል

አታፍሪም ዘለዓለም እርሱም ያከብርሻል

ከፍም ያደርግሻል አዎ

ድል ለነሣው ከጌታ ጋር በዙፋን ላይ ይቀመጥ ዘንድ ይሰጠዋል

መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ [1]

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ