Yosef Bekele/Baleweletayie Gieta/Weletaw Bezabegn
2005 · ትራክ 1 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ዛሬ ልጅ ተብዬ ክብርን አግኝቻለሁ
የቀድሞ ኑሮዬን ረስቼዋለሁ
ታሪኬን ለውጠህ ሰው አድርጐ አቆመኝ
የመረጥኩህ ልጄ እስራኤል ሆይ አለኝ
የመረጥኩህ ልጄ የምወድህ ሆይ አለኝ
አዝማች · Chorus
ኧረ ይህን ኢየሱስ ምን ብዬ ልባርከው
ውለታው በዛብኝ ከአይምሮዬም በላይ ነው
አቤት ምህረቱ ምን እከፍለዋለሁ
እኔም ክብር አግኝቼ አገልጋል ሆኛለሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
ይኸው ይድረስልኝ ዛሬም ምሥጋናዬ ኤሄሄ
ማለት ችያለሁኝ እኔም አባብዬ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በክርስትናዬ እድሜን ቆጥሬያለሁ
በልማዳዊ ሕይወት ተመላልሻለሁ
ዛሬ ግን ኢየሱስ ነፍሴ አወቀችህ
አምላኬ ጌታዬ ውዴ ነህ አለችህ
አምላኬ ጌታዬ አባቴ አለችህ
አዝማች · Chorus
ኧረ ይህን ኢየሱስ ምን ብዬ ልባርከው
ውለታው በዛብኝ ከአይምሮዬም በላይ ነው
አቤት ምህረቱ ምን እከፍለዋለሁ
እኔም ክብር አግኝቼ አገልጋል ሆኛለሁ
ቁጥር 4 · Verse 4
ይኸው እድረስልኝ ዛሬም ምሥጋናዬ ኤሄሄ
ማለት ችያለሁኝ እኔም አባብዬ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
የስጋዬን ሳስብ እንዲያው ስቅበዘበዝ
ጠላት ቤቴ ገብቶ ምርኮን ሲበዘብዝ
እርሱ ግን ጌታዬ አሰበኝ ለአንድ አፍታ
ኃይሌም ተመለሰ ጠላቴም ተረታ
ኃይሌም ተመለሰ ይክበር የእኔ ጌታ
አዝማች · Chorus
ኧረ ይህን ኢየሱስ ምን ብዬ ልባርከው
ውለታው በዛብኝ ከአይምሮዬም በላይ ነው
አቤት ምህረቱ ምን እከፍለዋለሁ
እኔም ክብር አግኝቼ አገልጋል ሆኛለሁ
ቁጥር 6 · Verse 6
ይኸው እድረስልኝ ዛሬም ምሥጋናዬ ኤሄሄ
ማለት ችያለሁኝ እኔም አባብዬ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ