ሃሌሉያ
Hallelujah
2005 · ትራክ 7 · 6:08 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ሃሌሉያ (ሃሌሉያ) (፬x)
ሃሌሉያ (ሃሌሉያ) (፬x)
ዛሬም ተመስገን/ተባረክ የእኔ ጌታ
ነገም ተመስገን/ተባረክ የእኔ አለኝታ
ሁሌም ተመስገን/ተባረክ ለዘለዓለም
እንዳንተ ያለ የለም አዎ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
እግዚአብሔር ኃያል ነህ ማንንም አትንቅም
ማስተዋል ጥበብህ አይመረመርም
ፍጥረት ሁሉ አንተን ሁሌ ያመስግኑህ
የሚፈሩህ ሁሉ ለአንተ ይገዙልህ (፫x)
አዝማች · Chorus
ሃሌሉያ (ሃሌሉያ) (፬x)
ሃሌሉያ (ሃሌሉያ) (፬x)
ዛሬም ተመስገን/ተባረክ የእኔ ጌታ
ነገም ተመስገን/ተባረክ የእኔ አለኝታ
ሁሌም ተመስገን/ተባረክ ለዘለዓለም
እንዳንተ ያለ የለም አዎ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ዙፋንህ ጽኑ ነው የማትነቃነቅ
ሽምግልና አያውቅህ ከቶ አትለዋወጥ
ጥንት እንደሰራኸው ዛሬም ትሰራለህ
አትደክም አትታክት አንተ ያው አንተ ነህ (፫x)
አዝማች · Chorus
ሃሌሉያ (ሃሌሉያ) (፬x)
ሃሌሉያ (ሃሌሉያ) (፬x)
ዛሬም ተመስገን/ተባረክ የእኔ ጌታ
ነገም ተመስገን/ተባረክ የእኔ አለኝታ
ሁሌም ተመስገን/ተባረክ ለዘለዓለም
እንዳንተ ያለ የለም አዎ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በሰማይ በምድር ከምድር በታች ሁሉ
ለታላቅነትህ ፍጥረታት ይስገዱ
ያመስግኑህ ዛሬ ያንግሱህ በዕልልታ
ንጉሥ ነህ ዘለዓለም የሰራዊት ጌታ (፫x)
አዝማች · Chorus
ሃሌሉያ (ሃሌሉያ) (፬x)
ሃሌሉያ (ሃሌሉያ) (፬x)
ዛሬም ተመስገን/ተባረክ የእኔ ጌታ
ነገም ተመስገን/ተባረክ የእኔ አለኝታ
ሁሌም ተመስገን/ተባረክ ለዘለዓለም
እንዳንተ ያለ የለም አዎ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ