በረኝነቱ
Beregnenetu
2017 · ትራክ 12 · 3:57 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በእረኝነቱ ተመርቻለሁ
ጠንቀቅ አድርጌም ድምፁን አውቃለሁ
በአረንጓዴው መስክ ባማረው ላይ
አንሰራፍቶኛል ሳይኖር ከልካይ
አልፈራም አውሬ ደፋር አርጎኛል
የአራዊት ድምፅ መቼ ያስፈራኛል
ባለመናወጥ ከምንጩ ልርካ
ከጭንቀት ማረፍ እንዲህ ነው ለካ
አዝማች · Chorus
እንዲህ ነው ለካ አሃ
እንዲህ ነው ለካ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ኧረ እንዴት ተለዪው ይሉኛል
ይህን የቅርብ ወዳጄን
ኧረ እንዴት ተለዪው ይሉኛል
ይህን የበረሃ ጓዴን
ኧረ እንዴት ተለዪው ይሉኛል
ይህን ሚስጢረኛዬን
ኧረ እንዴት ተለዪው ይሉኛል
ይህን መልካም እረኛዬን
አዝማች · Chorus
አልለየውም አልለየውም
ያለ እርሱ መኖር እኔስ አልችልም
አልለየውም አልለየውም
ያለ እርሱ ውበት ወዝም የለኝም (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ዝቅ ዝቅ ያልኩትን ያለ ከፍታዬ ከፍ ከፍ ያረገኝ
ወገን ያልሆንኩትን በልጁ ልጅ አርጎ ማዕረግን ያሳየኝ
የተደረገውን በጎነት ቸርነት አልችልም መሸከም
የምልህ የለኝም በሰጠኸኝ ዘመን ከፊት ፊቴ ቅደም
ብርታቴ እኮ ነህ ብርታቴ
ህይወቴ እኮ ነህ ህይወቴ
ጉልበቴ እኮ ነህ ጉልበቴ
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ለእኔ መድኃኒቴ (፪x)
መድኃኒቴ መድኃኒቴ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ